የመጀመሪያውን የኢቦላ በሽታ መከላከያ ክትባት በአለም የጤና ድርጅት WHO ተቀባይነት አገኘ

76
ኢዜአ ህዳር 3/2012 ኢቦላን ለመዋጋት  የመጀመሪያ እርምጃ ነው የተባለለት የመጀመሪያው የኢቦላ መከላከያ ክትባት በአለም የጤና ድርጅት ተቀባይነት ማግኘቱን ተነግሯል። ኢቨርቦ የሚል ስያሜ የተሰጠው የክትባት መድሃኒቱ በመርኪ ፋርማቲካል ኢንዱስትሪ የተመረተ መሆኑን የዘገበው ቢቢሲ ክትባቱ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሙከራ ሲደረግበት መቆየቱን ጠቅሷል። ክትባቱ በአለም አቀፉ የጤና ድርጅት ተቀባይነት ከማግኘቱ ጋር በተያያዘ አለም የኢቦላ መከላከያ መድሃኒት አግኝታለች ማለት እንደሚቻል ዘገባው አመልክቷል። እንደ  ዘገባው ይህ ክትባት ባለፈው አመት ወረርሽኙ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ  ለሁለት ጊዜ በተከሰተበት ሰዓት አገልግሎት ላይ ውሎ ነበር። ክትባቱ በሚቀጥለው ዓመት አጋማሽ ገበያ ላይ እንደሚውል ተገልጿ፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም