የነቀምቴ ስፔሻላይዝድ ሀፐስፒታል የማስፋፊያ ግንባታ እያካሔደ ነው

62
ነቀምቴ  ህዳር 3/2012  የነቀምቴ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እናቶችንና ሕፃናትን የተሻለ የሕክምና አገልግሎት የሚያገኙበት አማራጭ ለማስፋት በ37 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር ወጪ የማስፋፊያ ሕንፃ ግንባታ መጀመሩን አስታወቀ ። የነቀምቴ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በምስራቅ ወለጋና በነቀምቴ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች፣በሃይማኖት አባቶች፣መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች፣በባለሃብቶችና የአገር ሽማግለዎች ትናንት ተጎብኝቷል ። የነቀምቴ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ ዶክተር ታሪኩ ታደሰ በጉብኚቱ ወቅት እንደተናገሩት ሆስፒታሉ ወደ ስፔሻላይዝድ ያደገው በ2010 ዓ.ም ነው ። በምእራብ ኢትዮጵያ 11 ሚሊዮን ህዝብ የሚጠቀምበት ብቸኛ ሆስፒታል መሆኑን ስራ አስኪያጁ ገልፀው ሴቶችንና ህፃናትን የተሻለ የህክምና አገልግሎት የሚያገኙበት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር በ37 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር ባለ 4 ፎቅ የሕንፃ ግንባታ መጀመሩን ተናግረዋል። ሆስፒታሉ በ300 ሚሊዮን ብር ወጪ ዘመናዊነት የተላበሱ አዳዲስ ህንፃዎችን ለመገንባት የዲዛይን ስራ ማካሔዱን ገልፀው ወጪው በገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን ለመሰብሰብ ታቅዷል ። የምስራቅ ወለጋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳምሶን ቢራቱ እንደገለፁት ለስፔሻላይዝድ ሆስፒታሉ እድገትና በውስጡ ለሚከናወኑ የማስፋፊያ ስራዎች ህብረተሰቡን በማስተባበር አስተዳደሩ የድርሻቸውን ይወጣል ። የልማት ዋነኛ ተዋናይ የሆነው የህብረተሰብ ክፍል በበሽታ እንዳይጠቃ የቅድመ መከላከል ስራ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠውም አሳስበዋል ። ሼህ ሰይድ መሐመድ በበኩላቸው ሆስፒታሉ ከህብረተሰቡ ህይወት ጋር የተያያዘ በመሆኑ የሃይማኖት አባቶች ምእመናኑን በማስተባበር ተገቢው እገዛ እንዲደረግለት ይደረጋል ብለዋል ።          
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም