የአፋርና ኢሳ የሰላም ኮንፈረንስ በገዋኔ ወረዳ ይካሄዳል

52
ሰመራ ኅዳር 3 / 2012 የአፋርና ኢሳ የሰላም ኮንፈረንስ ነገ በገዋኔ ወረዳ እንደሚካሄድ የአፋር ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዩች ቢሮ ገለጸ። የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ አህመድ ከሎይታ ለኢትዮጵያ  ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት በሁለቱ ወንድማማች ሕዝቦች መካከል ሰላምና መግባባት ለመፍጠር የተዘጋጀው ኮንፍረንስ በእንድፍኦ ቀበሌ ይደረጋል። ኮንፍረንሱ በሕዝቦቹ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ታስቦ መዘጋጀቱን አስረድተዋል። እንዲሁም በግጭት መንስዔዎች ላይ በመምከር ዘላቂ መፍትሄ እንደሚያፈላልግ ሃላፊው ተናግረዋል። በኮንፈረንሱ ከ300በላይ የሚሆኑ ከፍተኛ አመራሮች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ወጣቶችና ሴቶች እንደሚሳተፉ አስታውቀዋል። በቀጣይም የሕዝቦቹን ግንኙነት የሚያጠናከሩ መድረኮች እንደሚካሄዱ አቶ አህመድ አስረድተዋል። እንዲሁም ሕዝቦቹን በመሠረተ ልማት ተቋማት ግንባታ ለማስተሳሰር ይሰራል ብለዋል። ባለፈው ወር አጋማሸ ተመሳሳይ የሰላም ኮንፈረንስ በሚሌ ወረዳ በአዳይቱ ከተማ መካሄዱ ይታወሳል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም