ዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስቀጠል እየሰራሁ ነው አለ

51

ኢዜአ ህዳር 3/2012  የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስቀጠል እየሰራ መሆኑን ገለጸ።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶክተር ለሚ ጉታ ዛሬ ለኢዜአ እንደተናገሩት በዩኒቨርሲቲው ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ለማረጋገጥ እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ ነው።

በዚህም ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመቀናጀት ተማሪዎች ትምህርታቸውን ለማስቀጠል እየተሰራ ነው ብለዋል።

ተማሪዎች ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው ወደ  ተቋሙ የመጡበትን ዓላማ  እንዲተዉ የሚገፋፏቸውን አካላት የፖለቲካ አጀንዳ ማስፈጸሚያ  እንዳይሆኑ ጥንቃቄ  እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

በዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ሂደቱ ሰላማዊነቱን ጠብቆ ለማካሄድ በከተማዋ ከተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ጋር በመሆን የተማሪዎችን ደህንነት  በመጠበቅ  ላይ እንደሚገኝ ፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም