ባለስልጣኑ ከ261 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ

80
ሶዶ ኅዳር  2 ቀን 2012  የወላይታ ዞን ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በሩብ ዓመቱ አስታወቀ። ጽህፈት ቤቱ  የሥራ አፈጻጸሙን  ገምግሟል። የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ `ሃላፊ አቶ መርሁን መንገሻ ጽህፈት ቤቱ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት 10 በመቶ ብልጫ ያለው ገቢ አስገብቷል። ገቢ ከዕቅድ አኳያም ቢሆን  የተሻለ መሆኑን ገልጸው፣ዞኑ ካለው አቅም አንጻር ግን መሰራት ይገባዋል ብለዋል። ግብር ከፋዩ ማህበረሰብ የሚጠበቅበትን ለመፈጸም ባሳየው ተነሳሽነት አከባቢያዊ ሰላምና  መረጋጋት ለገቢው ዕድገት ድርሻ እንደነበራቸው አስታውቀዋል። በዘርፉ የሚስተዋለው የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት፣የቅንነት መጓደልና አቅም ማነስ የወለዳቸው የመልካም አስተዳደር ጉድለቶች ለማረም ጥረት መደረጉን አስረድተዋል፡፡ በዞኑ ካሉት መዋቅሮች የተሻለ አፈጻጸም ካስመዘገቡት መካከል የሁምቦ ጠበላ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽህፈት ሃላፊ ወይዘሮ ትዝታ ተለሞስ ጽህፈት ቤቱ በከተማዋ ከመደበኛና ከማዘጋጃ ቤት ገቢ  ለመሰብሰብ ከእያንዳንዱ ባለሙያ ጋር ስምምነት ተደርጎ ወደተግባር መገባቱን ገልጸዋል፡፡ በዕቅድ የሚመራ ቁርጠኛ የሆነ አመራርና የሕዝብ ቅሬታዎች በፍጥነት ከተፈቱ ገቢውን መሰብሰብ ይቻላል ብለዋል። የአረካ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ይስሀቅ ፋልታሞ  ጽህፈት ቤቱ ከባለሙያዎችና ከሚመለከታቸው አካላት ባሳዩት የትኩረት ማነስ፣እርምጃ አለመወሰዱና ሥራው በብቃት ባለመመራቱ የሚፈለገውን ያህል ገቢ አለመሰብሰቡን ተናግረዋል ። በቀጣይም ክፍተቶችን በማረም በቀሪው ጊዜ የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል ። ጉባዔው የተሻለ አፈጻጸም ያሳዩትን የሁምቦ ጠበላ፣የቦዲቲ ከተማ አስተዳደርና የዳሞት ወይዴ ወረዳ ሸልሟል። የወላይታ ዞን ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በተያዘው ዓመት ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ አቅዷል።          
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም