የምስራቅ አፍሪካ ሴቶች የመንግሥት ሆስፒታሎችን ለወሊድ እንደማይመርጧቸው አንድ ሪፖርት ጠቆመ

81
ኢዜአ ህዳር 2/2012 በአፍሪካ የሚገኙ ሴቶች በወሊድ ጊዜ የሚከሰተውን የሞት ቁጥር ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት በመንግስት ከሚተዳደሩ ሆስፒታሎች የተሻለ እንክብካቤ እንደሚፈልጉ ሪፖርት ማመላከቱን ተንግሯል። በነጭ ሪባን ጥምረት የተደረገ ጥናት በኬንያ፣ በኡጋንዳ እና በታንዛኒያ የሚገኙ 300ሺ ሴቶች የመንግስት ሆስፒታሎች በወሊድ ጊዜ የሚሰጡት አገልግሎት እርካታ እንደማይሰጧቸው በመረጃው ተመላክቷል። ብዙዎቹ  በሕክምና ባለሙያዎች በሚደርስባቸው ስድብ እና ወከባ የተነሳ ከመንግስት ሆስፒታሎች እንደሚርቁ የተነገረ ሲሆን ይህ መሆኑ በመንግስት እና በሴቶች መካከል ያለውን ግንኙነት እንዳቋረጠ ተነግሯዋል። ሴቶች በዋነኝነት በሆስፒታሎች ውስጥ የተሻለ ንፅህናን አክብሮት እና እንክብካቤ መሻሻል እንዳለበት ጠቁመዋል። እንደ አለም ጤና ድርጅት በቀን ከእርግዝና እና ከወሊድ ጋር በተያያዘ ከ800 በላይ እናቶች እንደሚሞቱ ሲገልፅ ፤ከግማሽ በላይ ሞት የሚሆነው የተመዘገበው  ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት እንደሆነ በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡ በኬንያ ውስጥ ብቻ በግምት 22 ሴቶች በየቀኑ በወሊድ ወቅት በሚከሰቱት ችግሮች ምክንያት ይሞታሉ። አንዳንድ ቃለ መጠይቅ የተደረገላቸው ሴቶች  በመንግስት ሆስፒታሎች ቸልተኝነት ፣ የመሰረተ ልማት ችግር እና ከፍተኛ የህክምና ወጪዎች እንዳለ በጥናቱ ተመላክቷል  ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም