የመከላከያ ሠራዊት የመተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ ለዘመናዊ ሰራዊት ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው-መከላከያ ሚኒስቴር

868
አዲስ  አበባ  ጥቅምት 30/2012 የደንቡን መጽደቅ ተከትሎ የሠራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች የደንቡ መሻሻል አስፈላጊነትና ለሠራዊቱ ተልዕኮ አፈጻጸም ስላለው ፋይዳ መግለጫ ሰጥተዋል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ትናንት ባካሄደው 75ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ሲያሳልፍ አንዱ ጉዳይ የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ እንደነበር ይታወሳል። በዚህም የማቋቋሚ ደንቡን ማሻሻል አስፈላጊ በመሆኑ የመከላከያ ሚኒስቴር ረቂቅ ደንብ አዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ አቅርቦት ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ ከተወያየ በኋላ አንዳንድ ማሻሻያዎችን በማከል ደንቡ በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል። የደንቡን መጽደቅ ተከትሎ የሠራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች የደንቡ መሻሻል አስፈላጊነትና ለሠራዊቱ ተልዕኮ አፈጻጸም ስላለው ፋይዳ መግለጫ ሰጥተዋል። መከላከያም አገራዊ ለውጡን ተከትሎ ተቋሙን ለማሳደግና ለማዘመን እንዲሁም ጥንካሬውን ለማስቀጠልና ክፍተቶቹን የበለጠ ለመዝጋት የማሻሻያ ስራ ማከናወኑንም ገልጸዋል። የመከላከያ ሠራዊት ኢንዶክትሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል መሀመድ ተሰማ የመተዳደሪያ ደንቡ ከመጽደቁ በፊት መላው ሰዊት እንዲወያይበት መደረጉን አስታውሰዋል።  የደንቡ መሻሻል ለቀጣይ የሰራዊት ግንባታ ሂደት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል። የመከላከያ ሠራዊት ጥናትና ምርምር ማዕከል ሃላፊ ብርጋዴር ጄኔራል ተሾመ ገመቹ በበኩላቸው የመተዳደሪያ ደንቡ ማሻሻያ በአጠቃላይ በሶስት ጉዳዮች ላይ ትኩረት ማድረጉን ተናግረዋል። ብርጋዴር ጄኔራል ተሾመ አክለው እንደገለጹት፤ ከዚህ በፊት የነበረውን መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻል ያስፈለገበት ዋና ዓላማ ሰራዊቱ በብቃትና በውጤታማነት እንዲያገለግል ነው።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም