ዶክተር ሬክ ማቻር አዲስ አበባ ገቡ

54
አዲስ አበባ ሰኔ 13/2010 የደቡብ ሱዳን የተቃዋሚ ኃይል መሪ ዶክተር ሬክ ማቻር ዛሬ ማለዳ ላይ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ ለሁለት ዓመት ያህል ደቡብ የአፍሪካ የቆዩት ሬክ ማቻር አዲስ አበባ ሲገቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታዋ ሂሩት ዘመነ ተቀብለዋቸዋል። ዶክተር ሬክ ማቻር በዛሬው ዕለት በወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር ይነጋገራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ዶክተር አብይ በአገሪቷ ያለው ግጭት እንዲቆም የሚያስችል ውይይት ለማድረግ ዶክተር ሬክ ማቻርና የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫክር ማያሪዲትን ጋብዘዋቸዋል፡፡ ዶክተር አብይ ሁለቱ መሪዎች የደቡብ ሱዳናውያንን መፈናቀል፣ ሞት እና እንግልት እንዲያስቆሙ ይጠይቋቸዋል ተብሎም ይጠበቃል፡፡ የኢጋድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና የመሪዎች ስብሰባ በነገው ዕለት አዲስ አበባ ውስጥ እንደሚካሄድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የላከው መረጃ ያሳያል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም