በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም የፀረ-ኮሌራ ዘመቻ እየተከናወነ መሆኑ ተገለፀ

74
ጥቅምት 27/2012 የህክምና ባለሙያዎች በሱዳን በተቀሰቀሰው የኮሌራ በሽታ በርካታ ሰዎች ወደሚኖሩበትና ወደ ዋና ካርቱም እየተስፋፋ መምጣቱ ተጠቁሟል፡፡ የአገሪቷ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የቅርብ ጊዜ መረጃ እንደሚያሳየው በሽታው ከተቀሰቀሰበት ካለፈው መስከረም  2 ጀምሮ በኮሌራ ተይዘዋል ተብሎ የተጠረጠሩ ሰዎች ቁጥር 332 ሲሆን ስምንቱ መሞታቸውን  ነው የተነገረው፡፡ በኮሌራ በሽታ  ከተጠቁት ውስጥ ሁለቱ  ሰዎች የተገኙት በካርቱም  መሆኑ መረጃው ያሳያል፡፡ በሱዳን የአለም ጤና ድርጅት ተወካይ ዶክተር ነኢማ አል ጋስር የኮሌራ በሽታ መስፋፋት አረጋግጠዋል፡፡ በተለይ በዋና ከተማዋ ዙርያ በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ ላይ ከፍተኛ የመከላከል ስራ ካልተሰራ ትልቅ ጥፋት ሊያስከትል እንደሚችል አንስተዋል፡፡ የፀረ-ኮሌራ ዘመቻው በኢኮኖሚ ቀውስ፣በጎርፍና የመሳሰሉት ጫናዎች አመካኝነት ስራዎች በአግባቡ ማከናወን አለመቻሉም አንስተዋል፡፡ የአለም ጤና ድርጅት በሱዳን መንግስት በቀረበለት ጥያቄ መሰረት በሽታው በፍጥነት ሊሰራጭበት የሚችሉ ቦታዎች እንደ ሻርቅ ኢልኒል እና ኦምባዳ አካባቢዎች መሆናቸው ለይቷል ተብሏል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኮሌራና የተቅማጥ መድሃኒት በ5 መቶ የጤና አገልግሎት ሰጪ ፈጣን ተሸከርካሪዎች በማሰራጨት ላይ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ በተጨማሪም ከ1ሺህ 7 መቶ በላይ በጎ ፈቃደኞች ኮሌራ በሽታን እንዴት መከላከል እንደሚቻል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በማከናወን ላይ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ የአለም ጤና ድርጅት እንደሚለው አንድ ሰው በውሃ ወይም በምግብ አመካኝነት በኮሌራ በሽታ መያዝ አለመያዙ ማወቅ የሚቻለው ከ12 ሰዓታት እስከ 5 ቀን ነው፡፡ ምንጭ፡-ሲጂቲኤን አፍሪካ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም