በሶማሊያ ያጋጠመው የጎርፍ አደጋ ለበርካታ በሽታ መቀስቀስ ምክንያት እንዳይሆን ስጋት መፍጠሩ ተሰማ

86
ኢዜአ ጥቅምት 26/2012 የሶማሌ ቀይ መስቀል ማህበረሰብ ማክሰኞ እለት ያጋጠመው የጎርፍ አደጋ በሀገሪቱ የወባ በሽታ፣ተቅማጥና ሌሎች የኢንፌክሽን በሽታዎች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉ ስጋቱን ገለፀ፡፡ የሶማሊያ የቀይ መስቀል ማህበረሰብ አስተዳዳሪ አብዲ አብዱላሂ በለደወይን እንዳሉት ቀጣይ ሳምንት ከባድ ዝናብ ሊያጋጥም ይችላል በሚል በመቶ ሺዎች  የሚቆጠሩ ሰዎች መኖርያ ቀያቸው ለቀው ሄደዋል፡፡ ከአሁን በፊት ያጋጠመው የጎርፍ አደጋ የሰው ሂወት ቀጥፏል ወደ ፊት የሚመጣው የባሰ ጥፋት እንዳያስከትል ጥንቃቄ እንደሚያሻ ስጋታቸውን ገልጸዋል ፡፡ የሀገሪቷ ዋና ሆስፒታል እና ጤና ጣብያዎች በጎርፍ በመጥለቅለቃቸው ጎርፉን ተከትሎ ሊያጋጥሙ የሚችሉ በሽታዎች ከቁጥጥር በላይ ሊሆኑ እንደሚችሉ ሃላፊው ተናግረዋል፡፡ የሱማሌ ድጋፍ ሰጪ እንዳለው ጎርፉን ተከትሎ 50 የቀይ መስቀል በጎ ፈቃደኞች በበለድወይን ከተማ በመገኘት ድጋፍ በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ በጎፈቃደኞቹ ባለፈው ሳምንት በጎርፍ አደጋ ሂወታቸው ለፈ የሰባት ሰዎች አስከሬን ያወጡ ሲሆን ጀልባ በመጠቀም የ137 ሰዎች ህይወት መታደግ መቻላቸው ተነግሯል፡፡ ተንቀሳቃሽ ክለሊኒኮች ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ለመታደግ ከከተማዋ 10 ኪሎ ሜትር ርቃ ወደ ምትገኘዋ ኢልጃሌ በመውሰድ እርዳታ እንዲያገኙ መደረጉም ተገልጿል፡፡ የቀይ መስቀል ፕሬዝዳንት ዩሱፍ ሀስን ሞሐመድ በተቻለ አቅም የተጎዱትን ለመርዳት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ እንዳለና ተጎጂዎች ወደ ጤና ተቋማት ለመውሰድ በሚደረግ ጥረት ጎርፉ ስራቸውን አሰቸጋሪ እንዳደረገባቸው ይናገራሉ፡፡ በጥቅምት ወር በኢትዮጵያና በሱማሌ ተራራማ ቦታዎች የሚጥለው ከባድ ዝናብ ለአደገኛ ጎርፍ ምክንያት መሆኑም ጨምረው አብራርተዋል፡፡ (ሲጂቲኤን አፍሪካ)
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም