አሜሪካ ከፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ለመውጣት ፍላጎት እንዳላት ገለጸች

63

ኢዜአ፤ ጥቅምት 25/2012 አሜሪካ ከ2015 የፓሪስ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ለመውጣት ፍላጎት እንዳላት ለተባበሩት መንግስታት ድርጀት አስታወቀች ።

የአሜሪካ ከስምምነቱ የመውጣት እንቅስቃሴ በሌሎች የስምምነቱ አባል ሀገራት ስጋትንና ድንጋጤን ፈጥሯል።

አሜሪካ ከአለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ለመውጣት ያላትን ፍላጎት ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት በይፋ ያሳወቀችው ከአንድ አመት ሂደት በኋላ ሲሆን እንቅስቃሴው ከ2020 ሀገራዊ ምርጫ በኋላ ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

የፓሪሱ ስምምነት በ 2015 አሜሪካን ጨምሮ በ187 ሀገራት የተደረገ ሲሆን ዋና አላማውም ከኢንዱስትሪዎች የሚለቀቅ ጭስን በማስቀረት በአለም ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ አሳሳቢነቱ እየጨመረ የመጣውን የአየር ንብረት ለውጥ ብክለት ለመቀነስ እንደነበር ይታወሳል።

የአሜሪካ መንግስት ስምምነቱ በአሜሪካ ላይ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጫና እንዳሳደረ በተደጋጋሚ ሲገልፅ የቆየ ሲሆን፤ በዚህም ምክኒያት አሜሪካ ከስምምነቱ ራሷን እንደምታገል በዛሬው እለት ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት በፕሬዚዳንት ትራምፕ በኩል አስታውቃለች።

የአሜሪካ ከስምመነቱ የመውጣት እንቅስቃሴ የተጀመረው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስራቸውን በይፋ ከጀመሩበት እ.አ.አ ከ 2017 ጀምሮ እንደነበር የዘገበው ቢቢሲ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም