የናይጄሪያ  ፖሊስ በመስጊድ ውስጥ ታፍነው የነበሩ ሰዎችን  ነፃ አወጣ

104

ኢዜአ፤ ጥቅምት 25/2012 የናይጄርያ ፖሊስ በደቡባዊ ምስራቅ ኦዮ ግዛት ኢባዳን የሚገኝ መስጊድ ውስጥ ታግተው የቆዩት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ነፃ ማውጣቱ ተገለፀ፡፡

ታጋቾቹ ሰኞ እለት ነፃ የወጡት በአካባቢው ከሚገኝ ተቋም አምልጦ የወጣ አንድ የ17 አመት ታዳጊ በሰጣቸው መረጃ መሰረት መሆኑም ነው የተነገረው።

ፑንች የተባለ ጋዜጣ መረጃ እንደሚያሳየው  ድርጊቱ በዋነኝነት ያቀነባበረውና ሌሎች ስምንት ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የግዛቷ ፖሊስ ኮሚሽነር ሰሂና ኦሉኮሉ ጨምረው እንደገለፁት የተወሰኑ ተጎጂዎች ወንጀለኞቹ ቤተእምነቱን ለአመታት ለእንደዚህ አይነት ስራዎች በድብቅ ይጠቀሙበት እንደነበረ ገልፀዋል፡፡

በቦታው የነበረ ሁኔታ ኢሰብአዊ ድርጊቶችና ግድያዎች  ሲፈፀሙበት እንደነበረም ኮሚሽነሩ ይናገራሉ፡፡

ቦታው በበርካታ ሰዎች ዘንድ የሚታወቀው በአደንዛዥ እፅ እና ሱሶች ውስጥ ላሉ ናይጄርያውያን የማገገምያ ማአከል እንደሆነም ነው የተነገረው።

ተቋሙ በአሁኑ ሰአት አላማውን የሳተ ቢሆንም ቀደም ሲል በርካታ ሰዎች  ለቤተሰቦቻቸው ሃይማኖታዊ ድጋፍና ከሱስና አደንዛዥ እፅ ማገገምያነት እንደረዳቸው ምስክርነታቸው ሰጥተዋል፡፡ /ምንጭ፡-ቢቢሲ/

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም