የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤውን ነገ ያካሂዳል

92
ሰቆጣ (ኢዜአ) ጥቅምት 24 ቀን 2012ዓ.ም---የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ምክር ቤት 4ኛ ዙር 6ኛ ዓመት አራተኛ አስቸኳይ ጉባኤውን ነገ እንደሚያካሂድ የብሔረሰቡ አስተዳደር ምክር ቤት አስታወቀ፡፡ የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ኃይሉ ሚሰው ለኢዜአ እንደገለጹት በአስቸኳይ ጉባኤው በ2012 የትምህርት ዘመን አጀማመር እና በመስኖ ልማት እንቅስቃሴዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ ይመክራል። በብሔረሰብ አስተዳደሩ ስር ላሉ የተለያዩ ሴክተር መስሪያቤቶች አዳዲስ የመምሪያ ኃላፊዎች ሹመትያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተገልጿል። በተጨማሪም ምክር ቤቱ በብሔረሰብ አስተዳደሩ የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ በሰው እና በእንስሳት ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት አስቀድሞ ለመከላከል መከናወን ባለባቸው ተግባራት ላይ በመምከር አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ ታውቋል። ለአንድ ቀን በሚካሂደው በእዚህ አስቸኳይ ጉባኤ ላይ የተለያዩ ተቋማት የበጀት ዓመቱ ዕቅድ ቀርቦ እንደሚገመገምም ነው አቶ ኃይሉ የገለጹት፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም