ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አሕመድ ከሀዋሳ የተፈናቀሉትን ዜጎች ጎበኙ

111
ሀዋሳ ሰኔ 12/2010 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አሕመድ ሰሞኑን በሀዋሳ ከተማ በተከሰተው ግጭት ምክንያት ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለው በተለያየ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ዜጎችን ጎበኙ። ሰሞኑን የፊቼ ጨምበላላ በዓል አከባበርን ተከትሎ በሀዋሳ በተነሳው ግጭት በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን በርካታ ዜጎችም ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በየመጠለያ ጣቢያዎች መኖራቸው የሚታወቅ ነው። ይህንኑ በተመለከተ ህዝብ ለማወያየት በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በሀዋሳና በሶዶ ከተሞች በመገኘት ከህዝቡ ጋር ካደረጉት ውይይት መልስ ተፈናቃዮቹ ያሉበትን ሁኔታ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፤ አጽናንተዋቸዋልም። "ችግሩ የሚያልፍ በመሆኑ በሀዘንና በቁጭት ስሜት ራሳቸውን መጉዳት እንደማይኖርባቸውም" ገልጸውላቸዋል። መንግስትም ዜጎቹ በአፋጣኝ ወደ ቀደመ ህይወታቸው እንዲመለሱ የሚቻለውን ሁሉ ያደርጋል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም