ኢቫንካ ትራምፕ ሴቶችን ለማበረታት ወደ ሞሮኮ ሊያቀኑ ነው

62

ኢዜአ፤ ጥቅምት 21/2012 ኢቫንካ ትራምፕ የሴቶችን በኢኮኖሚያዊ ልማት ፕሮግራም ለማበረታታት እ.ኤ.አ 2019 ህዳር ወር መጀመሪያ  ሞሮኮን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

አሶሺዬትድ ፕሬስ እንደዘገበው በየካቲት ወር የተጀመረውን የሴቶችን ዓለም አቀፍ ልማት እና ብልጽግና ኢንሼቲቪ በታዳጊ አገራት ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለማድረግ የታሰበ ሲሆን ጉብኝቱ እ.ኤ.አ በ2019 ሲደረግ ለሶስተኛ ጊዜ ነው ተብሏል።

የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሴት ልጅ እና ከፍተኛ አማካሪ እ.ኤ.አ. 2019 ህዳር ወር መጀመሪያ የሰሜን አፍሪካ ሀገራትን እንደሚጎበኙ ከነጩ ቤተመንግስት የተገኘው መረጃ ያሳያል ሲል ነው ዘገባው ያሳየው።

የሞሮኮ መንግስት የዕርስት ህግን በማሻሻል ሴቶች ከወንዶች ግማሽ ያህል መውሰድ አለባቸው የሚለውን ህግ እንደሚደግፉም በትውተር ገፃቸው ገልፀዋል።

ኢቫንካ ትራምፕ  ከሚሊኒየም ፈተና ፈላጊ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጋር በመሆን  የታዳጊ አገራት የኢኮኖሚ ዕድገትን በማጎልበት፤ድህነትን ለመቀነስ  የሚረዱ  ገለልተኛ የአሜሪካ የውጭ እርዳታ ድርጅቶችን በመያዝ ወደ ሲያን ኬርክሮስ እንደሚያቀኑ ተጠቅሷል።

በቀጠናው ሴቶች ኢኮኖሚያዊ ነፃነት እንዲያገኙ እንዴት ማገዝ ይቻላል በሚለው ጉዳይ ዙሪያ ከህዳር 6 እስከ 8 ድረስ በሞሮኮ ዋና ከተማ ረባት እና ካዛብላንካ ከከፍተኛ ባለስልጣናት እና የአከባቢ መሪዎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሏል።

የሴቶች ዓለም አቀፋዊ ልማት እና ብልጽግና ተነሳሽነት በማደግ ላይ ባሉ አገራት ውስጥ የሚገኙ 50 ሚሊዮን የሚሆኑ ሴቶችን በኢኮኖሚያዊ እድገታቸው የመደገፍ ግብ አለው ተብሏል፡፡

በአሜሪካ መንግሥት የሚደገፍው እና በሥራ ቦታ ላይ የሴቶችን ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ የሚሰራው ፕሮጄክት ግቡ በሚቀጥሉት ስድስት ዓመታት ውስጥ እያደጉ ባሉ ሃገራት ውስጥ የሚኖሩ 50 ሚሊዮን ሴቶችን ተጠቃሚ ማድረግ ነው ተብሏል።

ኢቫንካ ትራምፕ ተነሳሽነቱን ለማሳደግ በሚያዚያ ወር ከሳሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራትን ኢትዮጵያ እና አይቮሪኮስትን ሲጎበኙ  እንዲሁም በመስከረም ወር  የደቡብ አሜሪካ ሀገራትን  አርጀንቲና ፣ ኮሎምቢያ እና ፓራጓይን እንደጎበኙ ይታወሳል ሲል ነው አሶሺዬትድ ፕሬስ የዘገበው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም