የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚ መሪ ሪክ ማቻር 'የደቡብ ሱዳን የጥምር መንግስት እንዲዘገይ ይፈልጋሉ' ተባለ

80
ጥቅምት 20/2012  የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚ መሪ ሪክ ማቻር የጥምር  መንግሥት ምስረታው ለስድስት ወራት እንዲዘገይ ጥሪ ማቅረባቸውን  ረውይተርስን ዋቢ በማድረግ ቢቢስ ዘግቧል፡፡ የሰላም ስምምነቱን ለመተግበር ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪይር “በጎ ፈቃደኝነት ይጎድላቸዋል” በማለት ክስ ማቅረባቸውንም መረጃው አስፍሯል፡፡ የቀድመው የአማፂ መሪ እና የሪክ ማቻር ቃል አቀባይ እስከ ህዳር 12 ቀን ድረስ ወደ አንድነት መንግሥት ለመቀላቀል እንደማይችሉ ገልፀዋል፡፡ ከወራት ውይይቶች እና የዲፕሎማሲ ግፊት  በኋላ በመስከረም ወር መስማማታቸው ይታወቃል ሲሉ ቃል አቀባዩ አስታውሰዋል። ወሳኝ የሁኑ ጉዳዩችን ቦታ በመስጠት ለመፍታት ተጨማሪ ስድስት ወር እንደሚያስፈልግ ቃል አቀባዩ አክለው ተናግረዋል። ይሁን እንጂ የሀገርቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አውት ደንግ አቹሊ ፕሬዝዳንት ኪር የሰላም ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ እና የአንድነት መንግስት እ.ኤ.አ ህዳር 12 2019 የመመስረት ፍላጎት አላቸው ሲሊ ለመንግስት ማስራጫ ጣቢያ መናገራቸውንም በመረጃው ተጠቅሷል ። የብሔራዊ አንድነት የተሃድሶ የሽግግር መንግሥት ለመመስረት ከሁለት ሳምንት ያነስ ጊዜ ይቀራል እናም  ከሁሉም አካላት ጋር በመፈራረም መንግስት ለመመስረት ፕሬዝዳንቱ በጣም ግልፅ እንደሆኑ ቢቢሲ የደቡብ ሱዳን ብሮድካስት ኮርፖረሽንን ዋቢ በማድረግ አስነብቧል። የተባበሩት መንግስታት የባለሙያዎች ቡድን መስከረም ወር እንዳስጠነቀቀው ሀገሪቱ የሰላም ስምምነቱን ለማበላሸት የምትፈቅድ ከሆነ ሀገሪቱ ወደ ሙሉ በሙሉ ግጭት ውስጥ የመግባት እድሏ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡ መንግስታትም ሆኑ የተቃዋሚዎች አማፂ ወታደሮች ከመንግስት ሠራዊት ጋር በማዋሃድ እና አገሪቱ ሊኖሯት የሚገባትን  ግዛቶች ብዛት ጨምሮ በሰላም ስምምነት ዝርዝር ጉዳይ ላይ አልተስማሙም ተብሏል፡፡ በስምምነቱ መሰረት ከሶስት ዓመት የሽግግር ጊዜ በኋላ ምርጫዎችን ለማካሄድ እንደተስማሙም ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም