በጭሮ ወረዳ ጥይቶችን ሲያጓጉዙ ተደርሶባቸዋል የተባሉ ግለሰቦች ተያዙ

66
ጭሮ  ጥቅምት 11 /2012፡- በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ጭሮ ወረዳ 2ሺህ  ጥይቶችን ሲያጓጉዙ ተደርሶባቸዋል ያላቸውን ተጠርጣሪ ግለሰቦች መያዞን ፖሊስ አስታወቀ። ግለሰቦቹ ጥይቶችን ሲጓጉዙ የነበረው ከሐረር ወደ አዲስ አበባ ለማስገባት እንደሆነ ተመልክቷል። የዞኑ ፖሊስ ወንጀል መርማራ የስራ ሂደት ቡድን  መሪ ዋና ኢንስፔክተር አብዱለዚዝ ጀማል  ለኢዜአ እንዳሉት ግለሰቦቹ የተያዙት ጥቅምት 9/2012ዓ.ም ምሽት አምስት ሰዓት አካባቢ ጥይቶቹን ኤፍስ አር በተባለ ተሽከርካሪ ጭነው በማጓጓዝ ላይ እንዳሉ ነው። በጭሮ ወረዳ አርበረከቴ የፍተሻ ጣቢያ ከጫኑት ጥይት ጋር ግለሰቦቹን በጣቢያው ሰራተኞችና በአከባቢው በሚገኙ የኦሮሚያ ፖሊስ አባላት አማካኝነት መያዝ ተችሏል። ከአሽከርካሪው ጋር በተጠርጣሪነት የተያዙት ግለሰቦቹ ሶስት እንደሆኑና ለህግ ለማቅረብም ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ የቡድኑ መሪ ጨምረው ገልጸዋል።          
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም