ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በሀዋሳ ህዝባዊ ውይይት እያካሄዱ ነው

59
ሀዋሳ ሰኔ 12/2010 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በሀዋሳ ከተማ ከህዝብ ጋር እየተወያዩ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህ የህዝብ ውይይት ሲባል ትናንት ማምሻውን ሀዋሳ ገብተው አድረዋል። በዛሬው ዕለትም ባሳለፍነው ሳምንት የፊቼ ጨምበላላ በዓል አከባበርን ተከትሎ ተከስቶ በነበረው ግጭት ዙሪያ ከህዝብ ጋር እየመከሩ ይገኛሉ። በውይይቱም የፌዴራል ፓርላማ አባላት፣ የክልሉ፣ የሲዳማ ዞንና የሀዋሳ ከተማ የስራ ኃላፊዎች፣ የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን እንዲሁም ከሲዳማ ዞንና ሀዋሳ ከተማ የተውጣጡ ወጣቶችና ሴቶች ይሳተፋሉ። ባለፈው ሳምንት የፊቼ ጨምበላላ በዓል አከባበርን ተከትሎ ተከስቶ በነበረው ግጭት በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወሳል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም