ታንዛኒያ ከካናዳው የወርቅ ማዕድን አውጪ ኩባንያ ጋር የነበረውን የቀረጥ ውዝግብ ፈታች

59
ኢዜአ፤ ጥቅምት 10/212 የታንዛንያ መንግስት ከካናዳው ባሪክ ጎልድ ካምፓኒ ጋር በብዙ ሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር ቀረጥ ጋር ተያይዞ የነበረው ውዝግብ  መፍታቱን ገለፀ፡፡ ካምፓኒው ያመረተው ምርት ወደ ውጭ እንዳይልክ ተከልክሎና ከፍተኛ የቀረጥ መጠን ተጥሎበት እንደነበረም ተጠቅሷል፡፡ ድርጅቱ 16 በመቶ የአክስዮን ድርሻ ለታንዛንያ መንግስት እንደሚሰጥ መስማማቱ ተገልጿል፡፡ በታንዛንያ ና ካምፓኒው በርካታ ዶላር ማጣት ምክንያት የነበረው አለመግባባትን ለመፍታት የተደረሰው ስምምነት ለሶስት አመታት እንደሚቆይ ተነግሯል፡፡ በታንዛንያ ጠቅላይ አቃቤህግ በኩል የፀደቀው ስምምነት መሰረት የታንዛንያ መንግስትና ካምፓኒው በጋራ በመሆን  ያቋቋሙት  ባለቤትነቱ የባሪክ የሆኑ በትዊጋ ሚነራልስ  ስር ያሉ ሶስት የማእድን ማውጫ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም