ምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤና አዋጆችን በማፅደቅ ጉባኤውን አጠናቀቀ

289

መቀሌ ኢዜአ ጥቅምት 9/ 2012 ዓም  የትግራይ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት 5ኛ ዘመን 17ኛ መደበኛ ጉባኤ የምክር ቤቱን ምክትል አፈ ጉባኤ ሹመትና አዋጆችን በማፅደቅ ተጠናቀቀ።

ጉባኤው ካጸደቃቸው አዋጆች መካከል ለክልሉ አርሶ አደሮች የግብርና ግብአቶች መግዥያ  የብድር ዋስትና፣ የክልሉ የዳኞች የክፍያ አሰራር መወሰኛ አዋጆች ይገኙበታል።

ጉባኤው ወይዘሮ ዘይነብ አብዱለጢፍ የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ እንዲሆኑ የቀረበውን ሹመትም በሙሉ ድምፅ በማፅደቅ ዛሬ ተጠናቋል።

በሁለት ቀን ቆይታው የክልሉ ስራ አስፈፃሚ፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ዋና ኦዲተር ፣ የትግራይ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲና የትግራይ መልሶ ማቋቋም ተቋምን የ2012 በጀት አመት የስራ እቅድ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል።