የአዕምሮ ጤና ህክምና ላይ የተሰማሩ ተቋማትና ባለሙያዎች በጤና ችግሩ ላይ ጠንካራ የምርምር ስራ እንዲያከናውኑ ተጠየቀ

70
ጥቅምት 08/2012 በኢትዮጵያ የአዕምሮ ጤና ህክምና ላይ የተሰማሩ ተቋማትና ባለሙያዎች በመስኩ ዙሪያ ጠንካራ የምርምር ስራዎችን ለማከናወን ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው ተገለጸ። የቅዱስ አማኑኤል የአእምሮ ህክምና ስፔሻላይዝደ ሆስፒታል ከጎንድር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባባር በተቀናጀ የህብረተሰብ  አዕምሮ ጤና አጠባበቅ ሙያ በሁለተኛ ዲግሪ ለ10ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን ባለሙያዎች ዛሬ አስመርቋል። በተቀናጀ የክሊኒካል የህብረተሰብ የአዕምሮ ጤና አጠባባቅ ዘርፍ ሰልጥነው ዛሬ ለመመረቅ የበቁት 25 ባለሙያዎች ሲሆኑ ሶስቱ ሴቶች ናቸው። ከተመራቂዎቹ መካከል የወርቅ ተሸላሚ የሆነው ኤኖክ አስፋው በዚህ ውቅት እንደገለጸው፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ የአዕምሮ ህክምንና ለመሻሻል የሚሰጠው ትኩረት እያደገ የመጣ ቢሆንም በቂ ትኩረት አይደለም። በአገሪቷ ያሉ የአእምሮ ህመም ታካሚዎች ብዙም ትኩረት የማይሰጣቸውና ህሙማኑን በተመለከተም በህብረተሰቡ ዘንድ ያለው ግንዛቤ አነስተኛ መሆኑን አመልክቷል። በመሆኑም የአዕምሮ ጤና ህክምና ላይ የሚሰሩ ተቋማትና ባለሙያዎች በመስኩ የምርምር ስራዎችን በማጠናከር አገልግሎቱን ለማስፋፋትና የህዝቡንም ግንዛቤ ማጠናከር አለባቸው ብሏል። የቅዱስ አማኑኤል ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ስራ አስኪያጂ  አቶ ኢዲኦ ፈጆ በዚህ ውቅት  እንዳሉት፤ ሆስፒታሉ  በተቀናጀ የክሊኒካል ህብረተሰብ - አቀፍ  አእምሮ  ጤና  ላይ ብቁ የሆኑ ሙያተኞችን ለአገርና ለወገን በማፈራቱ ደስተኛ ነው። ሙያተኖች በቀጣይ የስራ ጊዚያቸው ተመድበው በሚሰሩበት ተቋምና አካባቢ የአዕምሮ ጤና ግንዛቤና  አገልግሎት እንዲስፋፋ ጠንክርው እንዲሰሩ ለተመራቂዎቹ አደራ ብለዋል። የአዕምሮ ጤና ህክምና አገልግሎት በቂ ባለመሆኑ በአገሪቷ ከመጀመሪያ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ባሉት  ሆስፒታሎች 25 በመቶ ተደራሽ ለማድረግ  እንደሚሰራ ከጤና ጥበቃ የተገኘው መረጃ ያመላክታል ።                                          
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም