ምክር ቤቱ የአስፈጻሚ አካላት ስለጣንና ተግባር መወሰኛ አዋጅና የካቢኔ ሹመት አጸደቀ

92
ሀዋሳ ኢዜአ ጥቅምት 07/2012 ዓ.ም የደቡብ ክልል ምክር ቤት በ5ኛ ዙር 10ኛ መደበኛ ጉባኤ የተሻሻለውን የአስፈፃሚ አካላት ሥልጣንና ተግባር መወሰኛ አዋጅና የካቢኔ አባላትን ሹመት አፅደቀ፡፡ ምክር ቤቱ በዛሬው ውሎው የክልሉን የካቢኔ አባላት መልሶ ለማደራጀት ተሻሽሎ የቀረበውን የአስፈፃሚ አካላት ሥልጣንና ተግባር መወሰኛ አዋጅ አፅድቋል። በተጨማሪም ምክር ቤቱ  ባጸደቀው ሹመት ከዚህ በፊት 19 የነበረው የክልሉ ካቢኔ አባልት ቁጥር አዲሶቹን ጨምሮ ወደ 22 አድጓል። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው በአዲሱ አደረጃጀት ካቢኔዎችን ከሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ለማካተትና የሴት ካቢኔዎችን ተሳትፎ ለማሳደግ ጥረት መደረጉን ተናግረዋል ፡፡ በዚህ መሰረትም 1. አቶ ጥላሁን ከበደ ፡-በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የገጠር ልማት ዘርፍ አስተባባሪና እርሻና ተፈጥሮ ልማት ቢሮ ኃላፊ 2. ዶክተር ጌታሁን ጋረደው፡-በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ   ኃላፊ 3. አቶ ኃይለማርያም ተስፋዬ ፡ኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ 4. አቶ አክሊሉ ለማ ፡- የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኃላፊ 5. አቶ አንተነህ ፍቃዱ ፡- የውሀ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ 6. አቶ አቅናው ካውዛ ፡- የጤና ቢሮ ኃላፊ 7. አቶ ሀልገዮ ጅሎ ፡- የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊ 8. ወ/ሮ አስቴር ከፍታው ፡-  የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ 9. አቶ አብርሀም ማርሻሎ፡-በምክትል ርዕሰመስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊና የከተማ ዘርፍ አስተባባሪ 10. አቶ ማስረሻ በላቸው ፡-በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረት ልማት ዘርፍ አስተባባሪና የትራንስፖርትና መንገድ ቢሮ ኃላፊ 11. አቶ አለማየሁ ባወዴ ፡- በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ዘርፍ አስተባባሪና የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ 12. ወይዘሮ ወሰነች ቶማስ ፡-  የፕላንና ኮሚሽን ኮሚሽነር 13. አቶ ዘይኔ ቢልካ ፡- የእንስሳትና አሳ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ 14. ወይዘሮ ዘይቱና ኢብራሂም ፡- የገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር 15. አቶ ተዘራ ወልደማርያም ፡- የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ 16. አቶ ተፈሪ አባተ ፡- የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ 17. ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ ፡-የሳይንስ፣ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ 18. አቶ ምትኩ ታምሩ ፡- የአርብቶ አደር ጉዳዮችና ልዩ ድጋፍ ማስተባበሪያ ቢሮ ኃላፊ 19. ወይዘሮ ሂክማ ከይረዲን ፡- የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ 20. ወይዘሮ ሰናይት ሰለሞን ፡-የመንግስት ኮሚዪኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ 21. አቶ ስንታየሁ ወልደማርያም ፡- የባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ 22. አቶ ሙሉሰው ዘውዴ ፡- የጠቅላይ አቃቤ ህግ ኃላፊ ሆነው የተሸሙ ሲሆን አዳዲሶቹ የካቢኔ አባላት በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሐላ ፈጽመዋል፡፡    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም