የአውሮፓ ህብረት የሱዳንን የሽግግር መንግስት ለመርዳት ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ

61
ጥቅምት 5/2012 የአውሮፓ ህብረት  የሱዳንን የሽግግር መንግስት ባለስልጣናት ለመርዳት ቁልፍ አጋር ሆኖ እንደሚቀጥል ማስታወቁን ሲ ጂ ቲ ኤን ተናገረ፡፡ የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀ-መንበር አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን በሱዳን አዲሱን የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ሃላፊ አምባሳደር ሮበርት ቫን ደን ዶል መቀበላቸውን ዘገባው ጠቁሟል፡፡ አዲሱ አምባሳደር ዶል በሰጡት መግለጫም “የአውሮፓ ህብረትና አባል አገራቱ  ለሽግግር መንግስቱ ባለሥልጣናት ቁልፍ አጋር ለመሆን ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው"  ማለታቸውን መረጃው አክሏል፡፡ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር አራት የመንግሥት ሴት ሚኒስትሮችና በአፍሪካ የመጀመሪያዋን የፍትህ ሀላፊ በመሆን የተሾሙትን ግለሰብ በደስታ ተቀብለው ያነጋገሩ ሲሆን ‘’አዲሱ የሱዳን መንግስት ለወንዶች እና ለሴቶች እኩል መብት እንዲኖር ለማድረግ እያደረገ ያለው ከፍተኛ ጥረት ነው’’ ማለታቸው በመረጃው ተጠቅሷል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም