ሶማሊያ በአልሸባብ እጅ የነበሩ የጦር መሳሪያዎችን፣ በጎችንና ፍየሎችን በቁጥጥር ስር አዋለች - ኢዜአ አማርኛ
ሶማሊያ በአልሸባብ እጅ የነበሩ የጦር መሳሪያዎችን፣ በጎችንና ፍየሎችን በቁጥጥር ስር አዋለች
49
ኢዜአ፤ጥቅምት 5/2012 የሶማሊያ ጦር በሬይዳብ መንደር ባደረገው ኦፕሬሽን በአልሸባብ ስር የነበሩ 300 ፍየሎችን፣ በጎችን እና የጦር መሳሪያዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የጦሩ የሬዲዮ ጣቢያ አስታውቋል።
አልሸባብ እንስሳቱን ከአካባቢው ነዋሪዎች በኃይል አስገድዶ የወሰዳቸው እንደነበሩም ተነግሯል።
ኦፕሬሽኑን ያካሄደው ወታደራዊ ቡድን አዛዥ አሊ ሞሃመድ ሀሰን ለሬዲዮ ጣቢያው እንደተናገሩት በርካታ የአልሸባብ ታጣዊችም በቁጥጥር ስር ውለዋል።
አልሸባብ የሶማሊያን ማዕከላዊ መንግስት ለማውረድ ፅኑ ፍላጎት እንዳለውም ተገልጿል።
ለዚህም ለሚያካሂዳቸው ውጊያዎች ተሰግስጎ በሚገኝባቸው አካባቢዎች በሚኖሩ ሶማሊያውያን ላይ ታክስ እየሰበሰበ ነው ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው።