አልማ በክልሉ ልማት ላይ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ መሆኑን ገለፀ

167
አዲስ አበባ ጥቅምት 4 /2012  የአማራ ልማት ማህበር/አልማ / የተደራጀ ህዝባዊ አቅምን በመጠቀም ለክልሉ ህዝብ ዘላቂ የልማት ተጠቃሚነት እየሰራ መሆኑን ገለፀ ። የተደራጀህዝባዊአቅምንበመጠቀምየክልሉንህዝብዘላቂየማህበራዊናየኢኮኖሚያዊልማትተጠቃሚነትለማረጋገጥእየሰራእንደሚገኝየአማራአቀፍልማትማህበር /አልማ/ የስራአመራርቦርድሰብሳቢአቶተፈራደርበውገልፀዋል። ”ህዝባዊ ተሳትፎ ለዘላቂ ልማት” በሚል መሪ ሃሳብ የማህበሩ 13ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በባህርዳር ተከሔዷል። የቦርድ ሰብሳቢው አቶ ተፈራ ደርበው በጉባኤው ላይ እንደተናገሩት ማህበሩ የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚ ያደረጉ ፕሮጀክቶችን በመተግበር የመንግስትን የአቅም ክፍተት እየሞላ ይገኛል። በተለይም ማህበሩ የትምህርት፣ የጤና፣ የመንገድ፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ፣ የስራ ዕድል ፈጠራና ሌሎች የልማት ስራዎች ላይ በማተኮር በክልሉ ለመጣው ለውጥ የበኩሉን ድርሻ መወጣቱን ገልጸዋል። የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚ ያደረጉ የልማት ስራዎች እያከናወነ የሚገኘውም መላ ህዝቡን፣ አባላቱን፣ ባለሃብቱ፣ የልማት አጋሮችንና ደጋፊዎችን በማስተባበር መሆኑን ተናግረዋል። ማህበሩ በየጊዜው ተጨማሪ አዳዲስ አባላትን በማፍራት የክልሉን የመልማት ፍላጎት በራስ አቅም የመሸፈን አሰራርን ተከትሎ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል። ማህበሩ ከ2009 እስከ 2011 ዓ.ም በነበረው ጊዜ ውስጥ 313 የ1ኛና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት ለአገልግሎት ሲያበቃ በአሁኑ ጊዜ የ275 ትምህርት ቤቶች ግንባታ እያፋጠነ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በራስ አቅም የመልማት ፍላጎትን ለማሳካትም የአባላቱን ቁጥር ከ4 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ በማድረስ ከአንድ ቢሊዮን ብር የሚበልጥ ሃብት በመሰብሰብ ወረዳዎች በሰበሰቡት ልክ ችግራቸውን የሚፈቱበት አቅጣጫ መከተሉን ገልጸዋል። ባለፉት ዓመታት ማህበሩ ያከናወናቸው የልማት ተግባራት አመርቂ ቢሆንም "ካለው የልማት ችግር ስፋትና ጥልቀት አንፃር ሲታይ በቀጣይ የላቀ የልማት ስራ ማከናወን ይጠበቅብናል" ብለዋል። በተለይም የክልሉን የትምህርት ጥራት ችግር ለመፍታት ከ2012 እስከ 2014 የሚተገበር የለውጥ ስትራቴጂክ ዕቅድ ተግባራዊ ማድረጉን አስረድተዋል። ለሶስት ዓመታት በሚተገበረው የለውጥ ስትራተጂክ እቅዱ አሁን 16 በመቶ ላይ የሚገኘውን የትምህርት ቤቶች የጥራት ደረጃ ወደ 50 በመቶ ለማሳደግ ግብ ይዞ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። አልማ የክልሉን ልማት በራስ አቅም ለመፍታት የሚያስችል ራዕይ ቀርፆ በመንቀሳቀሱ በክልሉ ልማት ጉልህ አሻራውን አሳርፏል ያሉት ደግሞ በጉባኤው ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ነው። ማህበሩ በተለይ የትምህርት፣ የጤና ተደራሽነትና ጥራትን በማሻሻል ያካበተውን ልምድ በመጠቀም ህዝቡ የሚያነሳቸውን የልማት ስራዎች ለመመለስ አዲስ ዕቅድ ቀርፆ ወደ ተግባር መግባቱ ሊያስመሰግነው ይገባል ብለዋል። ዕቅዱን ለማሳካትም በክልሉና ከክልሉ ውጭ የሚገኙ ተወላጅ ባለሃብቶች፣ ዲያስፖራዎች፣ የልማት አጋሮችና ደጋፊዎች ርብርብ የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሉም አካል ትብብር እንዲያደርግ ጠይቀዋል። የክልሉተወላጅባለሃብትናየአልማየኮርፖሬትአባልኢንጅነርፀደቀይሁኔበበኩላቸው ከአሁን በፊት በገቡት ቃል መሰረት አንድአዳሪትምህርትቤትመገንባታቸውንገልጸዋል። ቤተሰቦቻቸው በማስተባበር በደሴ ከተማ ባስገነቡት ትምህርት ቤትም ስምንተኛ ክፍል ሚኒስትሪ ወስደው ከፍተኛ ውጤት ያመጡና ተሰጥኦ ያላቸው ተማሪዎች ገብተው እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ የሚማሩበት ነው ብለዋል። በቀጣይም የክልሉ ልማት እንዲፋጠን ራሳቸው ከሚያደርጉት አስተዋፅኦ ባለፈ ሌሎች ባለሃብቶች በአማራ ልማት ላይ አሻራቸውን እንዲያስቀምጡ በማስተባበር የታሰበው ዕቅድ እንዲሳካ እንደሚሰሩም አስረድተዋል። ጠቅላላጉባኤው ሊቀመንበርናየተጓደሉየስራአመራርአባላትንበመምረጥዛሬይጠናቀቃልተብሎይጠበቃል። በማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከ1ሺህ 300 በላይ በድምጽ የሚሳተፉናተጋባዥእንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል ።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም