የስንደቅ ዓላማ ቀን በአሶሳና በነቀምቴ ተከበረ

106
አሶሳ /ነቀምቴ /ኢዜአ ጥቅምት 03 / 2012 ዓ.ም. በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልልና በነቀምቴ ከተማ 12ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን ተከበረ ። አሶሳ ከተማ ላይ በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ጊቢ በተካሄደው የሰንደቅ ዓላማ ቀን ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና የከተማው የመንግስት ሠራተኞች ተሳትፈዋል፡፡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን፣ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ ሐብታሙ ታዬ በተገኙበት የፌደራልና የክልሉን ሰንደቅ ዓላማዎች የመስቀል ስነ-ስርዓት ተካሔዷል ፡፡ በስነ-ስርዓቱ ላይ ብሄራዊ መዝሙር የተዘመረ ሲሆን የክልሉ ፖሊስ አባላት እና ልዩ ሃይሎች ወታደራዊ ሰልፍ አሳይተዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በዓሉ በነቀምቴ ከተማ የመከላከያ ሰራዊት፣ሲቭል ማህበረሰብና የከተማው ነዋሪዎች  በተገኙበት “ሰንደቅ ዓለማችን የብዝሃነታችን ድምር ውጤትና የአንድነታችን ምሶሶ  ነው ” በሚል መሪ ቃል በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል ። የነቀምቴ ከተማ ምክር ቤት አፌ ጉባኤ ወይዘሮ ሳድያ አህመድ በበዓሉ ላይ እንደተናገሩት የሰንደቅ ዓለማ ቀን ስናከብር የተገኘውን የፖለቲካ ለውጥ በልማት በማስደገፍ ቀጣይነት እንዲኖረው የበኩላችን ድርሻ ለመወጣት ቃል የምንገባበት ቀን መሁኑን ማሰብ ያስፈልጋል  ብለዋል። ሰንደቅ ዓለማችን የሉዓላዊነታችን መገለጫና የሀገራችን ሕዝቦች በአንስ ጥላ ሰር የሚበሰቡበት መሆኑ ታውቆ ክብርና ሞገስ መስጠት አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል ። በመከላከያ ሰራዊት የምዕራብ እዝ አዛዥ ሜጄር ጀኔራል መሰለ መሰረት በበኩላቸው ሰንደቅ ዓለማ የአንድ ሀገር የማንነትና የሉዓላዊነት መገለጫ ነው ብሏል። ቅድመ አያቶቻችን ያወረሱን የሀገራችን ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ደወል ሆኖ እንዲቀጥል ሰራዊቱ ለሰንደቁ ተገቢውን ክብርና ጥበቃ እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል ።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም