ህዝቡ ለሀገር ሰላምና አንድነት በጋራ ሊቆም ይገባል--- አባገዳዎች

75
ነቀምቴ ኢዜአ ጥቅምት 3 ቀን 2012 ዓም ህዝቡ ለሀገር ሰላምና አንድነት በጋራ ሊቆም እንደሚገባ የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን አባገዳዎች አስገነዘቡ ። በዞኑ የኦዳ ቡሉቅ ኢሬቻ በዓል ትናንት ተከብሯል ። የኦዳ ቡሉቅ አባ ገዳ ደቻሣ ወዳጆ በስነ ስርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ኢሬቻ የአንድነት፣ የሠላም፣የፍቅርና የወንድማማችነት ተምሳሌት ነው ። በዓሉ ዘርና ሃይማኖት ሳይለይ ሁሉን በማሳተፍ የሚከበር መሆኑን ተናግረዋል ። ህዝቡም በዓሉን ሲያከብር በሀገሪቱ ሰላምና አንድነት እንዲሰፍን ፈጣሪውን በመለመንና ለተግባራዊነቱም በጋራ ቃል በመግባት ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል ። "ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ የዓለም የኖቤል ሠላም ተሸላሚ በሆኑበት ወቅት በዓሉ መከበሩ ከወትሮው ልዩ ያደርገዋል" ብለዋል። "በጠቅላይ ሚኒስተሩ የተገኘውን የሰላም ስኬት በማጠናከር ሀገራዊ ለውጡን ማስቀጠል ይገባል"ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል ። በአባገዳዎች ምርቃት የተጀመረው የበዓሉ አከባበር ስነ ስርዓት በሰላም ተጠናቋል ።        
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም