የአንድነት ፓርክ የአገራችንን ታሪክ በዓይናችን ያየንበት ነው - ታዳጊ ሕፃናት

74
ጥቅምት 2/2012 በታላቁ ቤተ መንግስት የተገነባውን የአንድነት ፓርክ የጎበኙ ታዳጊዎች ስንሰማው የቆየነውን የአገራችንን ታሪክ አሳይቶናል ሲሉ ተናገሩ። ከተለያዩ የመዲናዋ አካባቢዎች የተውጣጡ ታዳጊ ህፃናት ዛሬ የአንድነት ፓርክን ጎብኝተዋል። ታዳጊዎቹ ፓርኩ የአገሪቷን ታሪክ አሟልቶ የያዘና ኢትዮጵያዊነትን የሚያሳይ እንደሆነም ገልጸዋል። በታሪክና በወላጆቻቸው ሲነገራቸው የቆየውን አገራዊ ታሪክና ቅርስ በማየታቸው ደስተኞች መሆናቸውንም ተናግረዋል። ታዳጊዎቹ የጥንት አባቶች ያቆዩዋትን አገር እኛ ወጣቶች ተረክበን ለትውልድ የማስተላለፍ ኃላፊነት አለብን ሲሉም ተደምጠዋል። በተለይም በአሁኑ ወቅት ቅርሶችን መንከባከብ፣ አንድነትን ማስጠበቅና አገራዊ ስሜትን ማሳደግ እንደሚያስፈልግ ነው የተናገሩት።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም