ከአንድ ሺህ በላይ የጎዳና ተዳዳሪዎች አንድነት ፓርክን ጎበኙ

74
ጥቅምት 1/2012 ከአንድ ሺህ በላይ የጎዳና ተዳዳሪዎች አንድነት ፓርክን ጎበኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ ቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በጉብኝቱ ወቅት ተገኝተዋል። በታላቁ ቤተ መንግስት የተገነባው አንድነት ፓርክ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይና የተለያዩ የምስራቅ አፍሪካ አገራት መሪዎች  ባለፈው ሀሙስ ተመርቆ ስራ መጀመሩ ይታወቃል። በዛሬው እለት ከአንድ ሺህ በላይ የጎዳና ተዳዳሪዎች አንድነት ፓርክን በነፃ ገብተው እንዲጎበኙ ተደርጓል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በዚሁ ጊዜ እንዳሉትም የጎዳና ተዳዳሪዎች በይቻላል መንፈስ ባላቸው አቅም ከሰሩ አሁን ካሉበት ሁኔታ መውጣት ይችላሉ ብለዋል። በጉብኝቱ ላይ የተሳተፉት የጎዳና ተዳዳሪዎችም በጉብኝቱ መደሰታቸውንና እኩል ዜጋ በመሆን ለአገራቸው አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚችሉ የተረዱበት አጋጣሚ መሆኑን ተናግረዋል። ከቀትር በፊት ከምክትል ከንቲባው ጋር ከ2 ሺህ በላይ አረጋዊያንና አካል ጉዳተኞች ፓርኩን መጎብኘታቸው የሚታወስ ነው። ትናንት ከ4 ሺህ በላይ የሀገር መከላከያና የፖሊስ አባላት ፓርኩን መጎብኘታቸው ይታወሳል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም