ኢንጂነር ታከለ ኡማ አንድነት ፓርክን እየጎበኙ ነው

56
ጥቅምት 1/2012 የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከ2 ሺህ በላይ አረጋዊያንና አካል ጉዳተኞች ጋር አንድነት ፓርክን እየጎበኙ ነው። ፓርኩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይና የተለያዩ የምስራቅ አፍሪካ መሪዎች ጋር በመሆን ተመርቆ ስራ ጀምሯል። የፓርኩን ስራ መጀመር ተከትሎ በዛሬው እለት ምክትል ከንቲባው በጉብኝት ላይ ናቸው። ከምክትል ከንቲባው ጋር ከ2 ሺህ በላይ አረጋዊያንና አካል ጉዳተኞችም ፓርኩን በመጎብኘት ላይ ናቸው። የፓርኩን አጠቃላይ ይዘትና ገፅታ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምርቃቱ ዕለት ያብራሩ ሲሆን በተለይ ህብረ ብሄራዊ ለሆነችው ኢትዮጵያ የአንድነት ምሳሌ መሆኑም ተገልጿል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም