አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ የእንኳን ደስ ያለዎት መልእክት አስተላለፉ

91
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ የኖቤል ሽልማት አሸናፊ በመሆናቸው የእንኳን ደስ ያለዎት መልእክት አስተላለፉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ለኢዜአ በላከው መግለጫ የዩኒቨርስቲው ምሩቅ የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ የሠላም የኖቤል ሽልማት በማሸነፋቸው መደሰቱን ገልጿል፡፡ በሽልማቱ የተሰማውን ኩራት በዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ስም "እንኳን ደስ አለዎት" በማለት የደስታ በመግለጫውን አስተላልፏል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድ አባላት፣ ማኔጅመንትና ስታፍ ሰራተኞችም ዶክተር አብይ ዓለም አቀፍ የኖቤል ተሸላሚ በመሆናቸው የእንኳን ደስ ያለዎት መልእክት አስተላልፈዋል። የየክልሎች ርእሰ መስተዳድሮች እና ምክትል ርእሰ መስተዳድሮችም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የደስታ መግለጫ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም