መነሻውን ከኬኒያ ዊልሰን አየር መንገድ ያደረገው የሲለቨርስቶን አውሮፕላን ተከሰከሰ

73
መስከረም 30/2012 አውሮፕላኑ  ከዊልሰን አየር መንገድ ከተነሳ ከጥቂት ቆይታ በኋላ መከስከሱን መረጃዎች አመልክተዋል ሲል ሲ ጂ ቲ ኤን በዘገባው፡፡ የኬኒያው ስታንዳርድ ጋዜጣ 50 የሚሆኑ የውጪ ሀገራት  ተሳፋሪዎችን የጫነው አውሮፕላን በደረሰበት አደጋ ሳቢያ ከተሳፋሪዎቹ መካከልም ሁለቱ ላይ ጉዳት መድረሱን አስታውቋል፡፡ በርካታ ጉዳት የደረሰባቸው ተሳፋሪዎችም በአካባቢው የናይሮቢ ሰዓት አቆጣጠር 9፡00 ሰዓት አካባቢ በተለያዩ የከተማ ሆስፒታሎች መወሰዳቸውንም መረጃው ጠቁሟል፡፡ ሌሎች ሁሉን ተሳፋሪዎች ግን በጥሩ  ሁኔታ ከአውሮፕላን ውስጥ ማስወጣት መቻሉንም ዘገባው ያሳያል፡፡ በአደጋው ውስጥ ግን የሞተ ሰው ስለመኖሩ የሚያሳይ መረጃ አለመኖሩን ዘገባው አስፍሯል፡፡ ይፋዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነም አውሮፕላኑ የተከሰከሰው ከኬኒያዋ ዋና ከተማ ናይሮቢ በ303 ማይል ወይም ከሞምባሳ ወደብ በ488 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ነው ፡፡ በሲልቨርስቶን  የሚመራው ኩባንያ አውሮፕኑ  መከስከሱን የሚያሳይ የማረጋገጫ መግለጫ ማውጣቱንም መረጃው አስፍሯል፡፡ በመግለጫውም ሁኔታውን አስመልክቶ መፍትሄ ለማግኘት ከባለስልጣናት ጋር እየሰሩ መሆናቸውንም ዘገባው አክሏል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም