የኢጋድ አባል አገራት መሪዎች አዲስ አበባ ገቡ

62
መስከረም 29/ 2012 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አቢይ አሕመድ የአንድነት ፓርክን ምረቃ ለመታደም በኢትዮጵያ የተገኙትን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግሥታት (ኢጋድ) አባል ሀገራት መሪዎችን ተቀብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስር ዶክተር አቢይ አሕመድ የአንድነት ፓርክን ምረቃ ለመታደም በኢትዮጵያ የተገኙትን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግሥታት (ኢጋድ) አባል ሀገራት መሪዎችን ተቀብለዋል። የኡጋንዳ ሪፐብሊክ ፕሬዚደንት ዮዌሪ ሙሴቪኒ፣ የኬንያ ሪፐብሊክ ፕሬዚደንት ኡኹሩ ኬንያታ፣ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚደንት ሳልቫ ኪር፣ የፌዴራላዊት ሶማሊያ ሪፐብሊክ ፕሬዚደንት መሀመድ አብዱላሂ መሀመድ፣ የሱዳን ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ዛሬ አዲስ አበባ ከገቡት መሪዎች የሚጠቀሱ ናቸው። በተጨማሪም የጅቡቲ ሪፐብሊክ ልዑካን መሪ የሆኑት ናቢል መሀመድ አህመድም ተገኝተዋል። መሪዎቹ በታላቁ ቤተ መንግስት የተገነባውን የአንድነት ፓርክ ምረቃን ለመታደም መገኘታቸውም ታውቀዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም