የደቡብ ሱዳንና የሶማሊያ ፕሬዚዳንቶች አዲስ አበባ ገቡ

131
ኢዜአ፣መስከረም 29/2012 የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲትና የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ አዲስ አበባ ገብተዋል። ፕሬዚዳንቶቹ  ዛሬ  ረፋድ ላይ ቦሌ ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች አቀባባል አድርገውላቸዋል። ፕሬዚዳንቶቹ  አዲስ አበባ የገቡት በታለቁ ቤተ መንግስት በተገነባው የአንድነት ፓርክ ምረቃ ስነ ስዓት ላይ ለመሳተፍ ነው። የአንድነት ፓርክ የአረንጓዴ ስፍራ፣ የጥቁር አንበሳ ዋሻ፣ የአገር በቀል እጽዋቶች ስፍራ፣ የዘጠኙም        ክልሎች እልፍኞች፣ ታሪካዊ ህንጻዎችና ሙዚየም እንዲሁም የመካነ እንስሳት (ዙ) ያካተተ ስድስት የመስህብ ስፍራዎች አሉት። ከመስህብ ስፍራዎቹ መካከል የመጀመሪያዎቹ አምስቱ ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተመርቆ ለህዝብ ክፍት እንደሚሆን ተገልጿል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም