አለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ንቅናቄ  በአውስትራሊያ ተጀመረ

113

ኢዜአ፣ መስከረም 26/2012 የአየር ንብረት ለውጥ  እያስከተለ ያለውን ጉዳት በመቃወም በመላው የአውስትራሊያ ከተሞችና  በኒውዝላንድ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው፡፡

ኤኤፍፒ እንደዘገበው የተቃውሞው አላማ በአለም ዙሪያ ያሉ መንግስታት ለጉዳዩ ትኩረት እንዲጡና የመፍትሄ እርምጃዎች እንዲወስዱ  ለማሳሰብ  ነው፡፡

የሀገሪቱ ፓርላማ በሚገኝበት በሜልቦርን ከተማ ድምጻቸውን  ማሰማት  የጀመሩት ሰልፈኞች  ወደ ደቡብ አውስትራሊያ  ከተሞች አምርተዋል፡፡

በሌላኛዋ ከተማ ሲድኒም በመቶዎች የሚቆጠሩ የአካባቢ ተቆርቋሪዎች ወደ አደባባይ  በመውጣት የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰምተዋል፡፡

"ተቃውሟችን  መንግስት የአየር ብክለትና የስነም ህዳር መዛባትን ለመከላከል በቂ እርምጃ እስካልወሰደ ድረስ ይቀጥላል" ነው ያለው አውስትራሊያዊው የአየር ንብረት ተቆርቋሪ ጄን ሞርቶን፡፡

የንቅናቄውን አላማ የሚደግፉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎችም በዚሁ ሳምንት ይቀላቀላሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ያመላከተው ዘገባው በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት በአለም ዙሪያ ባሉ 60 ከተሞች የተቃውሞ ድምጽ ለማሰማት  እቅድ መያዙም ተጠቁሟል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም