ታዋቂው የሙዚቃ አቀናባሪ ኤሊያስ መልካ አረፈ

129
አዲስ አበባ ኢዜአ መስከረም 24/2012 የኢትዮጵያን ሙዚቃ ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረው እውቁ የሙዚቃ አቀናባሪ ኤሊያስ መልካ ከዚህ ዓለም ተለየ። በአዲስ አበባ አብነት አዲስ ከተማ አካባቢ የተወለደው ኤልያስ መልካ ባደረበት ህመም ትናንት ምሽት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተነግሯል። የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋችና አቀናባሪው ኤልያስ ለአንጋፋና ወጣት ድምፃዊያን በርካታ ሙዚቃዎችን አቀናብሯል። ኤሊያስ በስኳር ህመም ሲሰቃይ የነበረ ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ ኩላሊቱ መስራት አቁሞ እንደነበር የቅርብ  ወዳጆቹ ይናገራሉ። ኤሊያስ ሰሞኑን በኢትዮ-ጠቢብ ሆስፒታል ተኝቶ ህክምና ሲከታተል እንደነበረ ታውቋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም