ኢትዮጵያና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የ3 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ስምምነት አደረጉ

62
አዲስ አበባ  ሰኔ 8/2010 የኢትዮጵያና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የ3 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ስምምነት አደረጉ። የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች አልጋ ወራሽ ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አልናህያን በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው። በሁለቱ አገሮች መካከል ከተደረገው የ3 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት ውስጥ 2ቢሊዮኑ ኢንቨስትመንት ላይ የሚውል ሲሆን አንድ ቢሊዮኑ የባንክ ተቀማጭ እንደሚሆን ታውቋል። የተደረገው ስምምነት ለአገራዊ የኢኮኖሚ መዋቅር ሽግግር የራሱ የሆነ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር በተለያዩ ሰባት ዘርፎች በትብብር ለመስራት የሚያስችል ስምምነት አድርጋለች። ቱሪዝም፣ ዲፕሎማሲያዊ ቪዛ አገልግሎት፣ ኢኮኖሚያዊና ቴክኒካዊ ትብብር፣ እንዲሁም ባንክና ኢንቨስትመንት አገሮቹ በትብብር ለመስራት ከስምምነት የደረሱባቸው ጉዳዮች ናቸው። አልጋ ወራሽ ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አልናህያን በኢትዮጵያ እያደረጉት ያለው የስራ ጉብኝት ከፍተኛ የሆነ ዲፕሎማሲያዊ ውጤት የተገኘበት መሆኑን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም