የአልጄሪያ የጦር አዛዥ በሃገሪቱ የውስጥ ጉዳይ የሚገቡ የውጭ አካላትን አስጠነቀቁ

128
ኢዜአ መስከረም 21/2012 የአልጄሪያ መከላከያ ሚኒስቴር  በሀገሪቱ  ወቅታዊ የፖለቲካ ቀውስ ዙሪያ መግለጫ በሰጡበት ወቅት  ጠላት ያሏቸውን የውጭ የፖለቲካ አካላት  ማስጠንቀቂያ ሰጡ ሲል ዥንዋ አስነብቧል። የአልጀሪያ ጦር አዛዥ የሆኑት ጄኔራል አህመድ ጋይድ ሳህለ በምዕራብ ኦራን ግዛት የሚገኘውን  የጦር ሰፈር ለሁለተኛ ጊዜ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት በሰጡት መግለጫ  “ጠላት የውጭ ፓርቲዎች በአልጄሪያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት እየሞከሩ ነው” ሲሉም መናገራቸውን በመረጃው ሰፍሯል፡፡ ጋይድ ሳህላ የአውሮፓ ፓርላማ የሰብአዊ መብቶች ንዑስ ኮሚቴ በቅርቡ ያወጣውን መግለጫ በመጥቀስ እንደገለፁት የአልጄሪያ ባለስልጣናት በታህሳስ ወር ይካሄዳል ብለው ያሳለፉትን  ፕረዝዳንታዊ ምርጫ ውሳኔ የሚተች  እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በዚህም የአልጄሪያ ዜጎች የመንግስት ለወጥን በመፈለግ በየሳምንቱ የተቃውሞ ድምፅ እያሰሙ እንደሚገኙም ተገልጿል፡፡ እነዚህ አገሪቷን ወደ አለመረጋጋት እና የህዝቧን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል የታሰቡ ሙከራዎች ተስፋ አስቆራጭ እንደሆኑም  የጦር አዛዡ በገለፃቸው ጠቁመዋል፡፡ የጦር አዛዡ ቀጥለውም አልጄሪያዊያን የአገራቸው ባለቤት  በመሆናቸው  የራሳቸውን ውሳኔ የማድረግ መብት ያላቸው እነሱው ሲሆን  ከሌላ ማንኛውም አካል ምንም አይነት መመሪያ የማይቀበሉ ህዝቦችም ናቸው ብለዋል። ጋይድ ሳህለ በማከል  በአልጄሪያ እየተከናወነ ያለው  “የውስጥ ጉዳያችን የአልጀሪያዊያን ጉዳይ ብቻ  ነው ሲሉ  ተናግረዋል። የአልጀሪያ ህዝብ ነፃ፣ ፍትሃዊ እና ግልፅ የሆነ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በማካሄድ ከቀውስ የምንወጣበት ጊዜ እሩቅ አይደለም ብለዋል፡፡ የአልጄሪያ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት አብዲልቃድር በንሳህላ የአልጅሪያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እ.ኤ.አ በመጭው ታህሳስ 12 ወር እንደሚደረግ መስከረም ወር አጋማሽ ይፋ ማድረጋቸውን ዥንዋ በዘገባው አስታውሷል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም