የብሩንዲ ስደተኞችን የመመለስ ቀነ ገደብ ማብቃት ስጋት ፈጥሯል

57
ኢዜአ መስከረም 21/2012 በታንዛንያ መንግስት በተቀመጠው መርሃ ግብር መሰረት 220 ሺ የብሩንዲ ስደተኞችን በሃይል የማስመለስ ቀነ ገደብ እንዳበቃ መገለፁን ቢቢሲ በገፁ አስፍሯል። ሆኖም ግን በአካባቢው ያሉ ስደተኞችን ለመመለስ የሚያስችል ምንም ዓይነት  ምልክት አለመታየቱንም መረጃው ጠቁሟል፡፡ “ወደ ሃራችን ለመመለስ ዝግጁነት ሳይኖረን የታንዛንያ መንግስት በድንገት እንድንወጣ አዞናል”ሲል  ከስደተኞች አንዱ ሁኔታውን ለቢቢሲ አስረድቷል። የታንዛኒያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ካንጊ ሉጉላ ባሳለፍነው  ነሐሴ ወር ላይ “ስደተኞች ፍላጎት ኖራቸውም አልኖራቸው’’ የመመለስ እንቅስቃሴውን ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ዘገባው አስታውሷል፡፡ በደቡብ-ምዕራብ ታንዛኒያ በሦስት ካምፖች ውስጥ የተጠለሉት ስደተኞች ተቃውሞ በማሰማት ወደ ብሩንዲ እንመለሳለን የሚል ስጋት እንዳደረባቸው ዘገባው ጠቁሟል፡፡ አንዳንድ ስደተኞች ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ ከተደረገ   ህይወታቸው አደጋ ላይ ሊወድቅ እንደሚችልም ተናግረዋል። የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ የክልሉ ቃል አቀባይ ዳና ሂዩስ  የታንዛኒያ እና የቡሩንዲ መንግስታት ስደተኞችን ያለፍላጎት ከመመለስ እንዲቆጠቡ ኤጀንሲው መጠየቁን በዘገባው ተጠቅሷል ፡፡ በቀጣይ እ.ኤ.አ በ2020 ለሚካሄደው አጠቃላይ ሃገራዊ ምርጫ ተወዳዳሪ የሆኑ የቡሩንዲ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ላይ “ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት” እየተፈፀመ እንደሚገኝም በቅርብ ጊዜ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያወጣቸው ሪፖርቶች ያሳያሉ፡፡ የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ፒረር ኑኩርንዚዛ እ.ኤ.አ በ2015 ለሶስተኛ ጊዜ በሥልጣን ላይ ለመቆየት በሚያደርጉት ሂደት ሳቢያ የተከሰተው ፖለቲካዊ ቀውስ ያስከተለውን ውጤት ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማሳየት ፍላጎት እንዳላትም በመረጃው ተገልጿል። ሚስተር ሉጉላ የታንዛኒያ ስደተኞች በሀገራቸው በሰላም መኖር እንደሚችሉ ከተረጋገጠ  በኋላ ስደተኞቹን የመመለስ መብት  እንዳላትም ገልፀዋል  ብሏል ዘገባው፡፡      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም