የኤካ ኮተቤ የአዕምሮ ህክምና እና አጠቃላይ ሆስፒታል ዛሬ በይፋ ተመረቀ

66
መስከረም 20/2012 የጤና ሚኒስቴር በአዲስ አበባ ያስገነባው የኤካ ኮተቤ የአዕምሮ ህክምና እና አጠቃላይ ሆስፒታል ዛሬ በይፋ ተመረቀ። ሆስፒታሉ ዛሬ በተከናወነ ስነ-ስርዓት የተመረቀው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የጤና ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማንና ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው። ተቋሙ ከአእምሮ ህክምና ባሻገር ሌሎች አጠቃላይ የህክምና አገልግሎቶችንም ጎን ለጎን ይሰጣል። ሆስፒታሉ 350 አልጋዎች ያሉት ሲሆን 175 የሚሆኑት ለአዕምሮ ህሙማን አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው። ከሚያዚያ 2009 ዓ.ም አንስቶ ሥራ የጀመረው ሆስፒታሉ እስካሁን በአጠቃላይ ከ116 ሺህ ለሚልቁ 029 ታካሚዎች አገልግሎት ሰጥቷል። ከእነዚህ መካከልም 25 በመቶዎቹ የአእምሮ ህሙማን ናቸው።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም