በመብረቅ አደጋ የአንድ ሰው ሕይወት ሲያልፍ በአራት ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ

69
ጋምባሌ ኢዜአ መስከረም 19 / 2012 - በጋምቤላ ከተማ ትናንት በወደቀ መብረቅ የአንድ ሰው ሕይወት ሲያልፍ በአራት ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ቱት ኮርን ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት ጉዳቱ የደረሰው ትናንት በከተማው ከቀኑ 11፣00 ሰዓት አካባቢ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በቀበሌ 04 እና 05  በወደቀው መብረቅ ነው። በአደጋው የአንድ ሰው ሕይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በአራት ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል። የቆሰሉ ሰዎች በጋምቤላ ሆስፒታል ሕክምና የተደረገላቸው ሲሆን ከአንዷ ተጎጂ በስተቀር በአሁኑ ወቅት ሦስቱ የህክምና እርዳታ አግኝተው ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን ምክትል ኮሚሽነሩ ተናግረዋል። በደረሰው የመብረቅ አደጋ ሁለት የቀንድ ከብቶች መሞታቸውንም ምክትል ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም