በኢትዮጵያ  የቻይና የጨርቃ ጨርቅ አምራቾች ኢንቨስትመንት እድገት በማስመዝገብ ላይ ይገኛል

73
ኢዜአ መስከረም 14/2012 በኢትዮጵያ የቻይናውያን የጨርቃጨርቅ ዘርፍ አምራቾች ኢንቨስትመንት በፍጥነት እያደገ መምጣቱን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል። በቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ የተፈጠረላቸውን ዕድል በመጠቀም ቻይናውያኑ የግል የጨርቃ ጨርቅ አምራቾች በኢትዮጵያ የተሻለ የልማት ዘዴዎችን እያሰሱ እንደሆነ መረጃው ጠቁሟል። መቀመጫውን በቻይናዋ ጂንግሱ ክፍለ ሃገር ያደረገው ጂያንግሱ ሰንሻይን ግሩፕ እኤአ በ2016 በአፍሪካ ያፈሰሰውን መዋዕለ ንዋይ አስመልክቶ ባወጣው መረጃ ሰንሻይን ኢትዮጵያ የሱፍ ጨርቃጨርቅ ማምረቻ ፋብሪካን በ980 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወጪ በማድረግ በኢትዮጵያ መክፈቱን አስታውቋል። የድርጅቱ ዳሬክተር ዛሁ ጂያንግ ከሌሎች ሀገራት በተለየ ኢትዮጵያ የመረጡበትን ምክንያት ሲያስረዱ በአንጻራዊ  በአፍሪካ ከሌሎች ሀገራት የተረጋጋች እና ከ50 ሚሊየን በላይ የሚደርስ አምራች ሀይል ያላት መሆኑን ለሲጂቲኤን ተናግረዋል። ሰፊ የውሃና የሀይል አቅርቦት መኖሩ ምርቶቻቸውን ወደ አሜሪካና አውሮፓያለምንም ተጨማሪ ክፍያ መላክ መቻላቸው ተመራጭ እንዳደረጋት ጨምረው ገልጸዋል። እንደ ዛኦ ገለጻ በኢትዮጵያ በ2015 እኤአ ስራቸውን ሲጀምሩ መነሻ ያደረጉት ቤልት ኤንድ ሮድ ተነሳሽነት ያስቀመጠውን የሠራተኞች ክፍያ ጭማሪን እና ፖሊሲን  እንደሆነ አሳውቀዋል። የድርጅታቸው ፕሮጀክት ከብሔራዊ ልማት እና ማሻሻያ ኮሚሽን (NDRC) እና የንግድ ሚኒስቴር የይለፍ ካርድ ማግኘቱን ተናግረዋል። እንዲሁም ኢንቨትመንታቸውን ለማነቃቃት የንግድ ሚኒስቴር ድጋፎችንና ማበረታቻዎችን አድርጎልናል ብለዋል። እንደ ንግድ ሚኒስቴር  ከሆነ  በ2018 በዓለም ደረጃ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት /ኤፍ.ዲ.አይ./ፍሰት ለሦስት ተከታታይ አመታት በ29 በመቶ እየቀነሰ ቢሄድም የቻይና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ፍሰት ግን 143 ቢልየን ዶላር እንደነበር  በዚህም  ትልቋ ሁለተኛዋ  የወጭ ኢንቨስተር እንደነበረች ገልጸዋል። በ2018 መጨረሻ ላይ የቻይና  የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በ2002 ከነበረው በ66᎐3 በመቶ በማደጉ ከሁሉም ሀገራት እና ካለችበት ቀጠና  ከነበረችበት የ25ተኛ ደረጃ በማሻሻል የሦስተኛ ደረጃን እንድትይዝ አስችሏታል።በተመሳሳይ በዚህ ወቅት አፍሪካ በአለም ኢንቨስትመንት ከፍተኛ ፈተና አጋጥሟት የነበረ ቢሆንም  ጇንጉዙ ሰንሻይን ግሩፕ በኢትዮጵያ በ2018 ምርቱን በሦስት እጥፍ አሳድጎ ነበር። ዛኦ ለሲጂቲኤን  ሲናገሩ በኢትዮጵያ  በተደረገ  ዳሰሳ ጥናት በፋብሪካው ዙሪያ የሚኖሩ በርካታ ምላሾች  እምነት መሠረት ወደ ቻይና ሄደው ለመሰልጠንና ካልቻሉም በፋብሪካው ተቀጥረው ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው አሳይተዋል።እንደ ዛኦ ገለፃ ከሦስት ተከታታይ አመታት ተመራቂዎች ውስጥ 145ቱ ወደ ቻይና ለተጨማሪ ስልጠና የተላኩ ሲሆን የመጀመሪያዎቹ ሰልጣኞችም በያዝነው አመት መጋቢት ወር ላይ ይመለሳሉ። ሰልጣኞች መሰረታዊ ስልጠና በማግኘታቸው ተጨባጭ ለውጥ  ማምጣታቸውን እንዲሁም አብዛኛዎቹ የካምፓኒውን የአስተዳደር ሞዴል መቀበላቸውን እና በአንድ አመት ቆይታቸው በቻይና ህዝብ መልካምነት መደሰታቸውን እንደገለፁላቸው ተናግረዋል። አሁን ኢትዮጵያ እያስመዘገበች  ያለው እድገት ቻይና ሪፎርም ባደረገችበት እና እድገት ማስመዝገብ ከጀመረችበት ወቅት ጋር  ተመሳሳይነት እንዳለው አብራርተዋል።ከዚህ በተጨማሪ አዳዲስ ቴክኖሎጂና እና የአስተዳደር ዘዴዎችን እያስተዋወቁ እንደሚገኙ ተናግረው ይህም ከ70-80 በመቶ የሚሆኑትን ቻይናውያን በቀጣይ ሦስት አመታት ውስጥ በኢትዮጵያውያን የመተካት ስራ ለማከናወን እንደሚቻል አስረድተዋል ።ከዚህ ጎን ለጎን  ከተለይዩ ኮሌጆች ተመርቀው ወደ ፋብሪካው የሚቀጠሩ ተማሪዎች ደመውዝ በተመለከተ በሌሎች ተመሳሳይ ፋብሪካሰዎች ከሚከፈለው ከ40-50 በመቶ ጭማሪ እንዳለውም ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም