የሀዲያ ህዝብ ሰላምን በማስጠበቅ ሀገራዊ ለውጡን ከዳር እንዲያደርስ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጥሪ አቀረቡ

66
ሆሳእና  መስከረም 11/2012   የሀዲያ ህዝብ ጠብቆ ያቆየውን ሰላም በማስቀጠል ሀገራዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጥሪ አቀረቡ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከሆሳእና  ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ጋር ዛሬ ተወያይተዋል ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ  ወቅት እንደገለጹት ኢትዮጵያ የሁሉም ብሄሮች ሀገር በመሆኗ “ ትወልዱ ይህንኑ በማስቀጠል ለተተኪው ማስረከብ አለበት” ብለዋል፡፡ የሀዲያ ህዝብ ከሌሎች ብሄሮች ጋር በአንድነትና በመተሳሰብ የሚኖር ህዝብ መሆኑንም ተናግረዋል። ህዝቡ ሰላምን ለማስጠበቅ ያደረገው ትጋት ለአብሮነት ያለውን ትልቅ ቦታ ያሳየ መሆኑን ጠቅሰዋል። የህዝቡን መብት ለማስጠበቅ ሰላማዊና ፍትሀዊ የፖለቲካ ትግል ያደረጉና ለሀገሪቱ ዳር ድንበር መከበር መስዋዕትነት የከፈሉ ጀግኖች የወጡበት ምድር መሆኑን ተናግረዋል ። ህዝቡ ይህንን በማስቀጠል ሀገራዊ ለዉጡን ስኬታማ በማድረግ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ወጣቶች ጊዜያቸውን በአግባቡ በመጠቀምና ዉጪ ሀገር ሂዶ መስራትን ወደ ሀገር በመቀየር የለውጡ አካል መሆን እንዳለባቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት አስተላልፈዋል ።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም