የኢሬቻ የሠላም ሩጫ ተካሄደ

102
መስከረም 11/2012 ዛሬ በተካሄደው በታላቁ የ ኢሬቻ የሠላም ሩጫ ውድድር በወንዶች በሪሁ አረጋዊ በሴቶች ደግሞ ኦብሴ አብዴታ በአንደኛነት አጠናቀዋል ፡፡ ዛሬ በተካሄደው የኢሬቻ የጎዳና ሩጫ በወንዶች ከሱር ኮንስትራክሽን በሪሁ አረጋዊና በሴቶች ደግሞ ከለገ ጣፎ ለገ ዳዲ ከተማ ኦብሴ አብደታ በአንደኛነት በማጠናቀቅ የ50 ሺህ ብርና የዋንጫ ሽልማት ተበርክቷላቸዋል፡፡ በተጨማሪም ኃይለማርያም ኪሮስ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሁለተኛ ደረጃን፤ ደጀኔ ደበላ ደግሞ ከውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ሶስተኛ በመውጣት አሸንፈዋል፡፡ በሴቶች ደግሞ በግል መስተዋት ፍቅር ሁለተኛ ስትወጣ ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ አንቺዓለም ሃይማኖት ሶስተኛ በመሆን በተከታታይ በመግባት አሸንፈዋል፡፡ በዚሁ ውድድር 1ኛ ለወጡት የዋንጫና የ50 ሺህ ብር፤ 2ኛ ለወጡት ደግሞ 30 ሺህ ብር ሶስተኛ ለወጡት ደግሞ 20 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቷላቸዋል፡፡ መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ባደረገው ታላቁ የኤሬቻ የጎዳና ሩጫ 500 አትሌቶችና 50 ሺህ የጤና ሯጮች ተሳትፈዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም