የኢትዮጵያና የሩዋንዳ ብሄራዊ ቡድኖች ለነገው ጨዋታ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል

75
የኢትዮጵያና የሩዋንዳ ብሄራዊ ቡድኖች አመራሮች  ዛሬ  የሚካሄደውን ጨወታ አስመለክተው ዛሬ ማምሻውን መግለጫ ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብራህም መብራህቱና ቡድናቸው ከአምበሉ አስቻለው ታመነ በስተቀር በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል። የቡድኑ አባላት የአካል ብቃታቸውም ሆነ ስነ-ልቦናዊ ዝግጅታቸው በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የገለጹት አሰልጣኙ የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች በነቂስ ወጥተው ለብሔራዊ ቡድኑ ድጋፋቸውን እንዲሰጡ ጠቀዋል። የሩዋንዳው ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቨንሳንት ማሻሚ በበኩላቸው ነገ አስር ሰዓት ለሚካሄደው ውድድር ቡድናቸው በቂ ዝግጅት እንዳደረገ ተናግረዋል። የትግራይ ዓለም አቀፍ ስታዲየምም ደረጃውን የጠበቀና ለመጫወት ተስማሚ መሆኑን ገልጸው በመቀሌ ከተማ ለተደረገላቸው አቀባበል ምስጋና አቅርበዋል። የሁለቱም ብሄራዊ ቡድን ጨወታ ለሚገቡ ደጋፊዎችና ተጫዋቾች መግቢያ ባለ 100፤ባለ 50 እና 25 ብር ትኬት የተዘጋጀ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም