በጋምቤላ ክልል ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ የህዝቡ ሁለተናዊ ተሳትፎ እንዲጠናከር ተጠየቀ

59

ጋምቤላ ኢዜአ መስከረም 10/2012   በጋምቤላ ክልል ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የህዝቡ ሁለተናዊ ተሳትፎ እንዲጠናከር ተጠየቀ::

በክልሉ ኢታንግ ልዩ ወረዳ የሰላምና የልማት ህዝባዊ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው። ኮንፍረንሱ ዛሬ ሲጀመር የክልሉ ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ኡሞድ ኡጁሉ እንደሀገር ከመጣው ለውጥ ጋር ተያይዞ በክልሉ ተፈጥሮ የነበረው የተረጋጋ ሰላም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አልፎ አልፎ መጠነኛ የፀጥታ ችግሮች ተስተውለዋል። በተለይም በኢታንግ ልዩ ወረዳ በቅርቡ ፀጥታን ሊያደፈርሱ የሚችሉ ሁኔታዎች እንደታዩ ጠቅሰዋል። የክልሉ መንግስት ሀገራዊ ለውጡ የፈጠራቸውን ምቹ ሁኔታዎች በመጠቀም የህዝቡን ሁለተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል። እንደ ርዕሰ መስተዳደርሩ ገለጻ በተለይም በህዝቦች መካከል ያለውን አንድነት በማጠናከር የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥም ጥረት እየተደረገ ነው። በክልሉ ዘላቂ ሰላም በማስፈን የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ለማፋጠን በሚደረገው ጥረት ህዝቡ ተሳትፎውን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል ። ኮንፈረንሱ በህዝቦች መካከል ያለውን አንድነት ለማጠናከር የተጀመሩ ስራዎች አካል እንደሆነም አመልክተዋል። ለሁለት ቀናት በሚቆየው ኮንፍረንሱ አመራሮችን ጨምሮ ከወረዳው የተወጣጡ ከ250 በላይ ነዋሪዎች እየተሳተፉ ነው።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም