በአፋር ክልል የአርብቶ አደሮችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ አመራሩ በትጋት መስራት አለበት---አቶ አወል አርባ

63
መስከረም 9/2012 የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች በትጋት ሊሰሩ እንደሚገባ የአፋር ክልል ርዕሰ-መስተዳደር አቶ አወል አርባ አሳሰቡ:: በ2012 ዓ.ም እቅድ ዙሪያ ከወረዳ፣ ከዞን ከሴክተር መስሪያ ቤት አመራሮችጋር ዛሬ በሰመራ ከተማ ዉይይት አካሒደዋል። ርዕሰ-መለስተዳደሩ በውይይቱ ላይ አንደተናገሩት የክልሉ መንግስት የአርብቶ አደሩን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል የሪፈርምና የአመራር ለዉጥ አድርጎ እየሰራ ነዉ። ለውጡን የበለጠ ተቋማዊ ለመድረግና አስከታችኛው የአስተዳደር አርከን ድረስ አንዲዳረስ አደረጃጀቶችን ጭምር በመዘርጋት ህብረተሰቡ ለዘማናት ሲንከባለሉ የቆዩ የልማት ጥያቄዎችን ጥረት እየተደረገ ነው። “በመሆኑም በየደረጃዉ የሚገኙ አመራሮች የህብረተሰቡን ጥያቄ በአጭር፣በመካከላኛና በረጅም ጊዜ ለመመለስ የሚያስቸል ጥርት ያለ እቅድ አዘጋጅተው በበጀትአመቱ ወደ ስራ ሊገቡ የገባል”ብለዋል። በተለይም ህብረተሰቡን ከእቅድ እስከ አፈጻጸም ድረስ በማሳተፍ አንዲሁም በተቋማትም መካከል ቅንጅታዊ አሰራርን ባረጋገጠ አግባብ በቡድን አሰራር በመታገዝ መስራት እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል። ከተሳተፊዎች መካከል የአፋምቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሁሴን አሊ እንደገለጹት በቅርቡ የተደረገው የአመራር ለዉጥ ተከትሎ የህብረተሰቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ በሚዲያስችል መልክ እየተሰራ ነው። መድረኩ ሁሉም አመራር የትና ምን እየሰራ እንደሆነ ልምድ የሚለዋወጥበትና ከተናጥል ይልቅ በጋራ በቡድን መንፈስ የሚሰራበትን ሁኔታ የሚያመቻች እንደሆነም አስረድተዋል። የአዉሲረሲዞን አስተዳዳሪ አቶ አንዱ ያዮ በበኩላቸዉ በዞኑ የሚገኙ ወረዳዎች የህብረተሰቡን ጥያቄዎች እንደ ክብደትና አጣዳፊነት በማየት በቅደም ተከተል መመለስ የሚያስችሉ ተግባራትን ለማከናወን ስምምነት ላይ መደረሱን አስረድተዋል። በተጨማሪም የልማት ጥያቄዎች በመንግስት ዉስን ሃብት ብቻ ሊፈቱ ስለማይችሉ ህብረተሰቡን ያሳተፉ ተግባራትን ማከናወን ሌላኛው አማራጭ በመሆኑ በዞኑ ወረዳዎች ከሚገኙ ስምንት ወረዳዎች ጋር የጋራ አቋም መወሰዱን ጠቁመዋል። ዛሬ በተካሔደው የውይይት መድረክ ላይ ርዕሰ መስተዳደሩን ጨምሮ በክልሉ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም