ተሸላሚ ወጣቶችን ያሳፈረ መለስተኛ አውቶብስ ተገልብጦ ጉዳት አደረሰ

107
ሶዶ ሚያዝያ 27/2010 በወላይታ ሶዶ ከተማ ትናንት እውቅናና ሽልማት የተሰጣቸውን ወጣቶች አሳፍሮ ለመስክ ጉብኝት በጉዞ ላይ የነበረ መለስተኛ አውቶብስ ተገልብጦ ጉዳት ማድረሱን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ በአደጋው የአንድ ሰው ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በ11 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡ በአደጋው ህይወቱን ያጣው ወጣት በከብት ማድለብ ስራ ተሰማርቶ 600 ሺህ ብር ካፒታል በማፍራት ከዞኑ ወጣቶችና ስፖርት መመሪያ በዕለቱ እውቀናና የሜዳሊያ ሽልማት ተበርክቶለት ነበር። የወላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ዘውዱ ዘነበ ለኢዜአ እንደገለፁት አደጋው የደረሰው በእለቱ በሶዶ ከተማ አረካ መውጫ አካባቢ ሌላ መኪና ደርቦ ለማለፍ ሲሞክር ከፊት ለፊቱ የመጣበትን ተሸከርካሪ ሽሽት ለጎርፍ መውረጃ በተቆፈረ ቦይ ውስጥ በመግባቱ ነው። ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በወላይታ ሶዶ ክርሲቲያን ሆስፒታል ተኝተው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸዉ መሆኑን ምክትል ኮማንደሩ አሰታወቀዋል። የወላይታ ሶዶ ዞን ወጣቶችና ሰፖርት መምሪያ በስራ እድል ፈጠራ ከ300ሺህ እስከ 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ካፒታል ላፈሩ 75 ማህበራትና ኢንተርፕራይዞች ትላንት እውቅናና ሽልማት መስጠቱ ይታወሳ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም