በወላይታ ሶዶ ለ1 ሺህ 300 ህፃናት ድጋፍ ተደረገ

50
መስከረም 8/2012 በወላይታ ሶዶ ለ1 ሺህ 300 ችግረኛ ህጻናት ሙሉ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ፡፡ ድጋፉን ያደረጉት አለን ኢትዮጵያ የሰው ልጅ የለውጥ ማዕከልና የወላይታ በጎ ፈቃደኞች ማህበር አባላት ሲሆኑ ቁሳቁሱ ከተለያዩ አካላት የተሰበሰበ ነው፡፡ የአለን ኢትዮጵያ የሰዉ ልጅ የለዉጥ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ዘገዬ ዘዉዴ እንደገለፁት ማዕከሉ ላለፉት አራት ዓመታት በዞኑ የሚገኙ ችግረኛና አቅመ ደካማ ህጻናትና አረጋዊያንን የመደገፍ ስራ እያከናወነ ነው፡፡ በተለያዩ የኑሮ ችግሮች ምክንያት የትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ያጋጠመቸው ህጻናትን ለመርዳት ላለፉት 30 ቀናት ቁሳቁስ ሲያሰባስቡ መቆየታቸውን ገልጸዋል፡፡ በዚህምለ1 ሺህ 300 ህጻናትሙሉየትምህርትመማሪያቁሳቁስመደረጉንገልጸዉበገንዘብ ሲተመን ከ200 ሺህብርበላይየሚያወጣመሆኑንምተናግረዋል፡፡ ድጋፉ የመጠያየቅና የመደጋገፍ እሴቶችን በማጎልበት ማህበራዊ መስተጋብርን ከፍ እንደሚያደርግም አስረድተዋል፡፡ የወላይታ ዞን ሴቶች፤ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ መምሪያ ሃላፊ ወይዘሮ እቴነሽ ኤልያስ ማእከሉና በበጎ ፈቃደኞች ማህበር የተሰባሰቡት ወጣቶች ባከናወኑት ተግባር በርካታ ችግረኛ ተማሪዎችን ተጠቃሚ አድርጓል፡፡ ድጋፉ በአብዘኛዉ ከተማን ብቻ ማዕከል የሚያደርግ በመሆኑ የገጠር ነዋሪዎችም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ከእያንዳንዱ ወረዳ 60 የሚጠጉ ህጻናት ተመልምለዉ ድጋፍ እንደተደረገላቸዉ ገልጸዋል፡፡ በሶዶ ከተማ የዋዱ መንደር ነዋሪው አቶ መንግስቱ ቡቼ ካላቸው የኢኮኖሚ አቅም ማነስ የተነሳ ልጆቻቸዉን ትምህርት ቤት ለማስገባት ባልቻሉበት በአሁኑ ወቅት ድጋፍ ማግኘታቸው እንዳስደሰታቸዉ ተናግረዋል፡፡ ከኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ የተደረገለት የ7ኛ ክፍል ተማሪ ተስፋሁን ወርቁ በተደረገዉ ድጋፍ የተነሳ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማዉ ገልፆ በቀጣይ ዉጤታማ ለመሆን ለትምህርቱ ብቻ ትኩረት እንደሚሰጥ ተናግሯል፡፡      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም