የኢትዮጵያና የሱዳን የንግድ ፎረም መስከረም 17 ቀን 2012 ዓ.ም ይጀመራል

78
መስከረም 7/2012 የኢትዮጵያና የሱዳን የንግድ ምክር ቤት የሁለቱን አገሮች የንግድ ፎረም ከመስከረም 17 -19 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚያከናውን በሱዳን የሚገኙ ሚዲያዎች ዘግበዋል። በጉባኤው ላይ የተለያዩ የመንግስትና የግል የኢኮኖሚ ዘርፎች ፣ ባለሃብቶችና ኢንቨስተሮች እንደሚሳተፉበትም ተጠቅሷል። የጥምረቱ የንግድ ካውንስል ሰብሳቢ ዋጂድ ሜርጋኒ ፎረሙ የተዘጋጀው “ኢትዮጵያን እናመሰግናለን” በሚል መሪ ሀሳብ መሆኑንና ይህም ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይና እሳቸው በላኩት ልዩ ተወካያቸው በኩል ለሱዳን መረጋጋትና የሰላም ስምምነት መፈረም እንዲሁም ለአገሪቷ ህገ መንግስት ረቂቅ ዝግጅት ላደረገችው አስተዋጽኦ ምስጋና ለማቅረብ መሆኑን ተናግረዋል። የፎረሙ ዓላማ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን የኢኮኖሚና የንግድ ትብብር ከማሳደግ ባለፈ በአገራቱ የመንግስት ተቋማት ውስጥ ያለውን ተግዳሮት በመፍታት ለጋራ እድገት ለመስራትም ነው። የመንግስት ተወካዮችን፣ የገንዘብና ንግድ ሚኒስቴር ተጠሪዎችን፣ ነጋዴዎችንና የሁለቱን አገሮች የግል ባለሃብቶች በጉባኤው ይሳተፋሉ።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም